ሥለ አዲሱ የካቢኔ አባላት የሕዝብ አስተያየት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 8 2011ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ዓመታት ምክር ቤቱ በተደጋጋሚ የሴቶች ተሳትፎ በሚገባቸዉ ልክ እንዲሆን ጥያቄ ሲቀርብ በመቆየቱን ማስታወሳቸዉ ይታወቃል። 20 አባላት ያሉበት ከአዲሱ ካቢኔ 10ዎቹ ሴቶች ናቸዉ። በዚህም የሴቶች የአመራርን ሚና አጠናክሮ ለመቀጠል ሴቶች ከሌላ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ቁልፍ የሚንስትር ቦታዎችን እንዲይዙ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ መንግሥት የመከላከያ ሚኒስትር ሴት ናቸዉ። አዲሱን አካቢኔ ሹመት በተመለከተ የባሕርዳሩ ወኪላችን የሕዝብ አስተያየትን አሰባስቦ ልኮልናል።
አለምነዉ መኮንን
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ