1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞዴል ገሊላ በቀለ ማን ነች?

ሐሙስ፣ ግንቦት 13 2012

ገሊላ በቀለ በፋሽኑ ዓለም ሥመ ጥር ከሆኑ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ ነች። የፊልም ባለሙያ እና የበጎ አድራጎት ሰራተኛ ጭምር ነች። አብዛኛው ሕይወቷን በአውሮፓ እና በአሜሪካ መካከል ብታሳልፍም ወደ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ትጓዛለች። አሜሪካዊው የፊልም እና ቴሌቭዥን ባለሙያ ታይለር ፔሪ የገሊላ ፍቅረኛ ነው። አንድ ልጅም አላቸው።

https://p.dw.com/p/3cZe0
Frankreich | Äthiopisches Model Gelila Bekele
ምስል DW/H. Tiruneh

ሞዴል ገሊላ በቀለ ማን ነች?

ሞዴል ገሊላ በቀለ በዓለም አቀፍ የፋሽን መድረክ ተቀባይነት ካገኙ ጥቂት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ ነች። ገሊላ የተወለደችው አዲስ አበባ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ኑሮዋን በአሜሪካዋ ኒው ዮርክ አድርጋለች። የሞዴሊንግ ሙያ የጀመረችው የ17 አመት ታዳጊ ነበረች። በዛሬው የባሕል መድረክ መሰናዶ የፓሪሷ ሐይማኖት ጥሩነህ አነጋግራታለች። 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

ሐይማኖት ጥሩነህ
እሸቴ በቀለ