1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞስኮ-የሩሲያ ዉሳኔ፣የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት

ሰኞ፣ ግንቦት 24 2012

ሩሲያ በቅርቡ ያፀደቀችዉን መድሐኒት በመጪዉ ሳምንት ለኮቪድ 19 ሕሙማን መስጠት እንደምትጀምር አስታወቀች። ሮይተር ዜና አገልግሎት የሩሲያ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ፀረ ተሕዋሲዉ መድሐኒት በሽተኞችን ብቻ ሳይሆን በሩሲያ የጤና ስርዓት ላይ ያረፈዉን ጫና ለማቃለል ይረዳል።

https://p.dw.com/p/3d7E0
Indonesien | Eijkman Institut für Molekularbiologie forscht an einem Impfstoff für Corona
ምስል Eijkman Institute

ሩሲያ በቅርቡ ያፀደቀችዉን መድሐኒት በመጪዉ ሳምንት ለኮቪድ 19 ሕሙማን መስጠት እንደምትጀምር አስታወቀች። ሮይተር ዜና አገልግሎት የሩሲያ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ፀረ ተሕዋሲዉ መድሐኒት በሽተኞችን ብቻ ሳይሆን በሩሲያ የጤና ስርዓት ላይ ያረፈዉን ጫና ለማቃለል ይረዳል።የሮይተር ዘገባ የመድሐኒቱን ዓይነት፤የመፈወስ አቅሙንና ሙከራዉን ግን አልጠቀሰም።ይሁንና ጃፓን በተመሳሳይ መድሐኒት ላይ ሙከራ ማድረጓን አመልክቶ ቶኪዮ ለበሽተኞች ለመስጠት ገና አለመወሰኗን አስታዉቋል።የኮሮና ተሕዋሲ ባጭር ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት የተሰራጨባት ሩሲያ በተሕዋሲዉ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ከዩናያትድ ስቴትስና ከብራዚል ቀጥላ ከዓለም የሶስተኛነቱን ደረጃ ይዛለች።በተሕዋሲዉ በተያዙም፣ በኮቪድ 19 በሞቱም ሰዎች ቁጥር እስካሁን ዩናይትድ ስቴትስን የሚስተካከል ሐገር የለም።አሜሪካ 104,233 ዜጎችዋ በበሽታዉ ሞተዋል።1.8 ሚሊዮን አሜሪካዊ ደግሞ በተሕዋሲዉ ተለክፏል።ብራዚል ዉስጥ  30 ሺሕ ያሕል ሕዝብ ሲሞት፣ 515 ሺሕ የሚሆን ተለክፏል።ሩሲያ ዉስጥ ከ4 ሺሕ 600 መቶ በላይ ሲሞት፣ 406 ግድም ተለክፏል።በሟቾች ቁጥር የሶስተኛነቱን ደረጃ የያዘችዉ ብሪታንያ ናት።38 ሺሕ 500 ግድም።በመላዉ ዓለም በተሕዋሲዉ የተለከፈዉ ሰዉ ቁጥር ከ6.13 ሚሊዮን በልጧል፣ 370 ሺሕ 316 ሰዉ ሞቷል።

 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ