1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምሑራን «ድርድር» ስለሚባለው ምን ይላሉ?

ማክሰኞ፣ ኅዳር 8 2013

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እያደረጉት ያለው የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ በሕወሓት ላይ ሕግ የማስከበር ተግባር መጀመሯን ጎረቤት ሃገራቱ እንዲገነዘቡና ያልተፈለገ ግንዛቤ እንዳይዙ ይረዳል ሲሉ ሁለት የፖለቲካ ሳይንስ መምህራን ገለፁ።

https://p.dw.com/p/3lQQz
Stellvertretender Premierminister von Äthiopien - Demeke Mekonnen Hassen
ምስል G. Tiruneh

የፌዴራል መንግስት ድርድር እንደማይኖር ገልጧል

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እያደረጉት ያለው የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ በሕወሓት ላይ ሕግ የማስከበር ተግባር መጀመሯን ጎረቤት ሃገራቱ እንዲገነዘቡና ያልተፈለገ ግንዛቤ እንዳይዙ ይረዳል ሲሉ ሁለት የፖለቲካ ሳይንስ መምህራን ገለፁ።

በፌደራል እና በትግራይ ክልል መንግሥታት መካከል ድርድር ይካሄድ የሚሉ ዓለም አቀፍና ቃጣናዊ ድርጅቶችም ይሁን ሀገራት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውንና እየተካሄደ ያለውን በትክክል ያልተገነዘቡ ናቸው የሚሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፣ የድርድር ጊዜው ማለፉን ገልጠዋል። ይልቁንም በሕግ ማስከበር ተግባሩ ውስጥ ሰብዓዊ ቀውስ እንዳይከሰት ከውጪ ሆነው ሊከታተሉ ነው የሚገባቸው ብለዋል።

ሕወሓት ወቅታዊው ችግር በፖለቲካ መፍትሔ እንዲያገኝ ደጋግሞ የጠየቀ ቢሆንም የፌዴራል መንግስት በበኩሉ ድርድር እንደማይኖርና የመጨረሻ የተባለው ሕግ የማስከበር ተግባር በቀጣይ ቀናት እንደሚከናወን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዐስታውቀዋል። 

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ