1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተቋማት እንቅስቃሴ ተቋርጧል

ዓርብ፣ የካቲት 22 2011

በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ሌሎች ተቋማት ሥራ እንዳልጀመሩ የአይከል ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ፖሊስ በበኩሉ የአካባቢው ሰላም እየተሸሻለ በመሆኑ የተዘጉ ትምህርት ቤቶችም እየተከፈቱ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

https://p.dw.com/p/3EKI8
Äthiopien - Gonder
ምስል DW/A. Mekonnen

«ከ50,ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል»

በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ሌሎች ተቋማት ሥራ እንዳልጀመሩ የአይከል ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ደግሞ በ4 ወረዳዎች ከ50,000 በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡ ፖሊስ በበኩሉ የአካባቢው ሰላም እየተሸሻለ በመሆኑ የተዘጉ ትምህርት ቤቶችም እየተከፈቱ እንደሆነ አመልክቷል፡፡
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአይከል ከተማ ነዋሪ በስልክ ለDW እንደገለፁት  ከትቂት ወራት በፊት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የሰላም መደፍረስ ምክንት ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም፡፡
ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ካቆሙ ወራት ማስቆጠራቸውን ፣ ከአካባቢ ሚሊሺያዎች በስተቀር ህብረተሰቡንም ያወያዬ አካል እንደሌለና በትራንስፖርት በኩል መሻሻል መኖሩን አብራርተዋል፡፡ የማዕካለዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን እርካብ በበኩላቸው ከቅማንትና ከአማራ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ መምህራን ተፈናቅለዋል፣ ተማሪዎችም ተበትነዋል ብለዋል፡፡ በዋናነት ችግሩ ተፈጠረባቸውን ወረዳዎችንም በዝርዝር አስቀምጠዋል፡፡

አቶ መስፍን አያይዘውም በክልልና አገር አቀፍ ደረጃ ሊፈተኑ የነበሩ ተማሪዎችም እስካሁን ለፈተናዎቹ መቀመጥ የሚያስችላቸውን ፎረም እንዳልሞሉ ነው ተናገሩት፡፡ችግሩን ለመፍታት ከአገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅትና ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋርእየተነጋገሩ እንደሆነ የተናገሩት አቶ መስፍን ተማሪዎቹና ወላጆች በሚደርሱበት ስምምነት መሰረት ወይ የመካካሻ ትምህርት ወስደው ይፈተናሉ አለበለዚም ፈተናው በልዩ ሁኔታ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዛወር ይደረጋል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጅዓለም በበኩላቸው በተፈጠረው አንፃራዊ ሰላም አንዳንድ ትምህርት ቤች እተከፈቱ መሆኑን ጠቅሰው በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረውን ቀውስ ወደነበረበት ለመመለስ እተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
 

ዓለምነው መኮንን
ነጃት ኢብራሒም
ማንተጋፍቶት ስለሺ