1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ማንነትን መሰረት ያደረገ እስር አለተፈፀመም» መንግሥት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 28 2014

ህወሓት በአፋር እና አማራ ክልሎች አሰቃቂ የጅምላ ግድያዎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከመፈፀም አልፎ የሕዝብ እና የመንግሥት ንብረቶችን ማውደሙን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት ገለፀ። የደረሰው ጉዳት ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/43x3v
Äthiopien | PK Billene Seyoum | Sprecherin des Premierministers
ምስል Yohannes Geberegziabher/DW

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መግለጫ

 

ህወሓት በአፋር እና አማራ ክልሎች አሰቃቂ የጅምላ ግድያዎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከመፈፀም አልፎ የሕዝብ እና የመንግሥት ንብረቶችን ማውደሙን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ገለፀ። የደረሰው ጉዳት ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ይህንን የህወሓትን የጥፋት ድርጊት ዓለም አቀፍ ተቋማት በዝምታ ማየታቸውም አጠያያቂ ነው ተብሏል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማንነትን መሰረት ያደረገ እስር አለመፈፀሙን የገለፀው መንግሥት አሜሪካን ጨምሮ ጥቂት አገሮች በኢትዮጵያ ማንነትን መሰረት ያደረገ እስር አለ ማለታቸውን አጣጥሎ ውድቅ አድርጎታል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ