1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መጪው ምርጫ እና የፀጥታው ይዞታ በኦሮሚያ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 8 2013

በኦሮሚያ ክልል መጪው ምርጫ የፀጥታ እክል እንዳይገጥመው ሰፊ የሰላምና ፀጥታ ማስከበር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ። ይሁንና በክልሉ ከሚንቀሳቀሱት ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ኢዜማ ከሌሎች ክልሎች አንጻር በኦሮሚያ ክልል የማደርገው እንቅስቃሴ አዳጋች ሆኖብኛል ነው ያለው።

https://p.dw.com/p/3s8RS
Karte Äthiopien englisch

የምርጫ ዝግጅትና የፀጥታ ስጋት

በኦሮሚያ ክልል ቀጣዩ ብሔራዊ ምርጫ 2013 የፀጥታ እክል እንዳይገጥመው ሰፊ የሰላምና ፀጥታ ማስከበር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የፀጥታ አማካሪ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት አሁናዊ የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ የተሻለ ደረጃ ላይ መሆኑን አመልክተው አልፎ አልፎ የሚደመጡ የሰላም እጦት ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አዳጋች በሆነ በሽምቅ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሚቀሰቀስ ነው ብለዋል። ይሁንና በክልሉ ከሚንቀሳቀሱት ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከሌሎች ክልሎች አንጻር በኦሮሚያ ክልል የማደርገው እንቅስቃሴ አዳጋች ሆኖብኛል ነው ያለው። በኦሮሚያ አራቱ የወለጋ ዞኖች ባለው የፀጥታ ስጋት እስካሁን የመራጮች ምዝገባን በመርሃግብሩ መከወን አለመቻሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰሞኑን አስታውቋል።

ስዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ