1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መጠነ ሰፊው እስር፤ የመንግስት ማብራሪያና የባለሞያ አስተያየት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 16 2014

የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን «የሕግ የበላይነትን የማስከበር» ባለው ርምጃ በርካቶች ለእስር እየተዳረጉ ነው። የመንግሥትን ርምጃ የጅምላ እስር በሚል የሚተቹ በርካቶች ናቸው። የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ሂደቱ በዋናነት ታጥቋል ያሉት ኢመደበኛ ቡድን እና ትስስር ያላቸው ያሏቸው አካላት ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4Bn0Y
Äthiopien | Dr. Legesse Tulu - Kommunikationsminister
ምስል Seyoum Getu/DW

የጅምላ እስር በሚል የሚተቹ በርካቶች ናቸው

የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን «የሕግ የበላይነትን የማስከበር» ባለው ርምጃ በርካቶች ለእስር እየተዳረጉ ነው። የመንግሥትን ርምጃ የጅምላ እስር በሚል የሚተቹ በርካቶች ናቸው። የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ስለጉዳዩ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ማብራሪያ ሂደቱ በዋናነት ታጥቋል ያሉት ኢመደበኛ ቡድን እና ትስስር ያላቸው ያሏቸው አካላት ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል። አስተያየት ሰጪዎች መንግስት አንድን ቡድን ዓልሞ ለመምታት ያቀደው ስልት ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሲሰጡ ይደመጣል። አንድ የሕግ ባለሞያ በፊናቸው መንግስት የሚወስዳቸው የትኛውም ርምጃዎች ውጤት የሚያመጡት ሕጋዊ ሂደታቸውን ከተከተሉ ብቻ ነው ብለዋል። 

ሥዩም ጌቱ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ