1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥትንና ሸማቂ ቡድንን የማስታረቅ ጥረት

ሐሙስ፣ የካቲት 26 2012

ኮሚቴው በአራቱ የምዕራብ ኦሮሚያና ጉጂ ዞኖች ላይ እርቅ ወርዶ ከሚመሩበት ወታደራዊ እዝ እንዲወጡ፣ በሲቪል አስተዳደር ስር እንዲገቡም እሰራለሁ ብሏል።የክልሉ መንግስት ይህንን ጅምር በበጎ እንደሚመለከተው እና ኮሚቴው የወጠነውም እንዲሳካ ፍላጎቱ መሆኑን ለ ዶቼ ቬለ አሳውቋል።

https://p.dw.com/p/3Yvmh
Äthiopien Medien Briefing Friedensgespräche West-Oromia
ምስል DW/S. Muche

መንግሥትንና ሸማቂ ቡድንን የማስታረቅ ጥረት

በምዕራብ ኦሮሚያ በመንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሸማቂ ተዋጊ ባለው ቡድን መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት ራሱን "ፍርቱ" ብሎ የሰየመ የእርቅ እና ሰላም ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራ መጀመሩን ዛሬ አስታወቀ። ኮሚቴው በአራቱ የምዕራብ ኦሮሚያና ጉጂ ዞኖች ላይ እርቅ ወርዶ ከሚመሩበት ወታደራዊ እዝ እንዲወጡ፣ በሲቪል አስተዳደር ስር እንዲገቡም እሰራለሁ ብሏል።የክልሉ መንግስት ይህንን ጅምር በበጎ እንደሚመለከተው እና ኮሚቴው የወጠነውም እንዲሳካ ፍላጎቱ መሆኑን ለ ዶቼ ቬለ አሳውቋል።ፍርቱ የእርቅ እና ሰላም ኮሚቴ በመንግስት እና በሸማቂ ተዋጊዎች አለመግባባት ምክንያት በህዝቡ ላይ የደረሰው እና እየደረሰ ነው ያለው እንግልት እንዲቆም የማቀርበውን የእርቅ ጥሪ በማይቀበለው ላይ የተለመዱ ዓለም አቀፍ የቅጣት ተሞክሮዎች እንዲተገበሩ ጫና አደርጋለሁ ብሏል።የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ