መንግሥት የቬንትሌተር እጥረትን እንዲፈታ ተጠየቀ
ሰኞ፣ መጋቢት 28 2012ማስታወቂያ
መንግስት በኮሮና ተኅዋሲ ለሚጠቁ ጽኑ ህሙማን እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የትንፋሽ መስጫ መሳሪያ እጥረት በቻለው አቅም እንዲፈታ ጥሪ ቀረበ። ኢትዮጵያ ይህ ቬንትሌተር የሚባለው መሳሪያ ብዙም እንደሌላት እና ያለውም ለኮሮና ተጠቂዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች በሽታዎች ጽኑ ህክምና ውስጥ ለገቡትም እንደሚውል የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ተናግሯል። የመሳሪያው ዋጋ ውድ ቢሆንም አሁን ከተለያየ ወገን ወረርሽኙን ለመከላከል ከሚገኘው ድጋፍ ለዚሁ እቃ ግዥ ቢውል የሚል የባለሙያዎች ምክርም ጎልቶ እየተደመጠ ነው።ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ