1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥት በኢትዮጵያ «ረሃብ የለም» ሲል ገለጸ

ማክሰኞ፣ ጥር 11 2013

የተባበሩት መንግታት የዓለም ምግብ መርሃ ግብር እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች ትግራይ ውስጥ የረሃብ አደጋ ተደቅኗል ብለዋል። በብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መንግሥት ስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን በመጥቀስ «ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰአት ረሐብ የለም» ብሏል።

https://p.dw.com/p/3o8af
Pressebild Red Cross, Rotes Kreuz | Äthiopien Tigray, Hilfe
ምስል ICRC

«ኢትዮጵያ ዉስጥ ረሃብ የለም» የኢትዮጵያ ብሔራዊ አደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

የተባበሩት መንግታት የዓለም ምግብ መርሃ ግብር እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች ትግራይ ውስጥ የረሃብ አደጋ ተደቅኗል ቢሉም መንግሥት ተገቢውን ርዳታ እያደረገ መኾኑን ዐስታወቀ። በብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መንግሥት ስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን በመጥቀስ «ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰአት ረሃብ የለም» ብሏል። በብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ፦ የምግብ እህሎችን በትግራይም ሆነ በቤኒሻንጉል አካባቢ ለተፈናቃዮች ሁሉ እየደረሰ በመሆኑ በአሁን ሰዓት ረሃብ እየተባለ የሚነገረዉ ነገርም ሆነ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ተርቧል ብሎ ለመናገር የሚያስችል ነገር የለም ብለዋል። ኃላፊው ይህን ያሉት ሰሞኑን የተለያዩ የውጭ ብዙኃን መገናኛዎች፣  የዓለም የምግብ ድርጅት እና የውጭ የርዳታ ድርጅቶችን ጠቅሰዉ በትግራይ የረሃብ አደጋ ተደቅኗል፤ አደጋው ሕጻናት ላይ የጠና ነው ሲሉ የተለያዩ ዘገቦችን ማስነበባቸውን በተመለከተ ከዶይቸ ቬለ (DW) ለቀረበላቸው ጥያቄ ነው። በትግራይ «በሕግ ማስከበር ዘመቻው» ለተፈናቀሉ 485 ሺህ ሰዎች የሚሆን  ሰማንያ ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ኩንታል የምግብ ርዳታ መንግሥት ማቅረቡን ኃላፊው አክለው ተናግረዋል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ