1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥት ስለ ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትና ህወሓት ወታደራዊ ጥምረት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 6 2013

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በማለት የሚጠራው እና በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ኃይል ከህወሓት ኃይሎች ጋር ወታደራዊ ጥምረት ፈጥሬያለሁ ብሏል።በዚህ ላይ መልስ እንዲሰጥ የተጠየቀው መንግሥት በበኩሉ «ይህንን ቀድሜ ነው የማውቀው» ሲል መልሷል።የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ጥምረቱ የተለየ ጫና እና ግፊት እንደማይፈጥርባቸውም ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3yuij
Äthiopien | Getachew Balcha
ምስል Seyum Getu/DW

ስለ ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትና ህወሓት ወታደራዊ ጥምረት የመንግስት ምላሽ

  •  

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በማለት የሚጠራው እና በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው ቡድን ከህወሓት ኃይሎች ጋር ወታደራዊ ጥምረት ፈጥሬያለሁ ብሏል።በዚህ ላይ መልስ እንዲሰጥ የተጠየቀው መንግስት በበኩሉ «ይህንን ቀድሜ ነው የማውቀው» ሲል መልሷል። የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ከዶይቼ ቬለ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጥምረቱ የተለየ ጫና እና ግፊት እንደማይፈጥርባቸውም ተናግረዋል። ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል።

Taye Dendea
ምስል Geberu Godane

ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ