1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥት ህወሓት ለቀቅኳቸዉ ያላቸዉ ሰዎች የጦር ምርኮኞች አይደሉም አለ

ሰኞ፣ ግንቦት 15 2014

የትግራይ ባለሥልጣናት ከ4 ሺህ በላይ የጦር ምርኮኞች ለቀናል ማለታቸዉን የፌዴራል መንግሥት አስተባብሏል። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እንደተናገሩት "በተለያየ መልኩ ወደ ትግራይ ክልል ውስጥ ለሥራ ፍለጋ የሄዱ፣ እና ሕወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች ተቆጣጠራቸው በነበሩ አካባቢዎች የያዛቸው ናቸው " ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4BkbN
Äthiopien | Dr. Legesse Tulu - Kommunikationsminister
ምስል Seyoum Getu/DW

የትግራይ ባለሥልጣናት ከ4 ሺህ በላይ የጦር ምርኮኞች ለቀናል ማለታቸዉን የፌዴራል መንግሥት አስተባብሏል። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎትሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ሕወሓት ለቀኩዋቸዉ ስላለዉ ሰዎች እንደተናገሩት "በተለያየ መልኩ ወደ ትግራይ ክልል ውስጥ ለሥራ ፍለጋ የሄዱ፣ ህወሓት ከዚህ ቀደም ለፀጥታ ያሰጉኛል በሚል የሰበሰባቸው፤ መከላከያ ሠራዊት መቀሌን ለቆ ሲወጣ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ያገታቸው ኃይሎች እና ሕወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች ተቆጣጠራቸው በነበሩ አካባቢዎች የያዛቸውና በማስገደድ በተለይ ምሽግ ሲያስቆፍራቸው የነበሩ፣ የራሱን ታጣቂዎች ትጥቅ ሲያጓጉዝባቸው የነበሩ ዜጎች ናቸው " ብለዋል።

"እንዚሁን ሰዎች መቀሌ በመውሰድ የቀድሞውን የመከላከያ ሠራዊት መለዮ በማልበስ ምርኮኞች ናቸው በሚል ያቀረባቸው ናቸው" ሲሉም ነዉ ሚኒስትሩ ለዶቼ ቬለ የተናገሩት። የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ መንግሥት ይህንን ምርኮኞች ተለቀቁ የሚለውን ዜና ባስተባበለ ማግሥት "አሁንም ከተለቀቁት በእጥፍ የሚልቁ የጦር ምርኮኞች በትግራይ መንግሥት እጅ ውስጥ እያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ምርኮኞች መለቀቃቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለመካድ መሞከሩ ከንቱነት ወይስ የውሸት ልማድ" ሲሉ የምንግሥትን ምላሽ አጣጥለውታል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሰ