1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈናቃዮች እሮሮ

ሰኞ፣ ግንቦት 12 2011

ከዚህ ቀደም በዚህ ጣቢያ የነበሩ ተፈናቃዮች ሲመለሱ እንዲቀሩ መደረጋቸውን የተናገሩት ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው እነዚሁ ተፈናቃዮች እንደሚሉት ከዛሬ ሦስት ወር አንስቶ ሰብዓዊ እርዳታ ተቋርጦባቸዋል። ከመካከላቸው ንብረታቸው መውደሙን የሚገልጹት ተፈናቃዮች ደግሞ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/3InAA
Äthiopien Vertriebene Menschen in Mendi
ምስል DW/N. Dessalegn

መንዲ የሚገኙ ተፈናቃዮች እሮሮ

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዳሊቲ ከተሰኘው አካባቢ ተፈናቅለው በምዕራብ ወለጋ መንዲ የተጠለሉ ተፈናቃዮች ሰብዓዊ እርዳታ በመቋረጡ ለችግር ተዳርገናል ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል። ከዚህ ቀደም በዚህ ጣቢያ የነበሩ ተፈናቃዮች ሲመለሱ እንዲቀሩ መደረጋቸውን የተናገሩት ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው እነዚሁ ተፈናቃዮች እንደሚሉት ከዛሬ ሦስት ወር አንስቶ ሰብዓዊ እርዳታ ተቋርጦባቸዋል። ከመካከላቸው ንብረታቸው መውደሙን የሚገልጹት ተፈናቃዮች ደግሞ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጠይቀዋል። ዶይቼ ቬለ ስለ ተፈናቃዮቹ አቤቱታ የምዕራብ ወለጋ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር እና የመንዲ ከተማ ሃላፊዎችን ለማነጋገር ቢሞክርም ሊያገኛቸው አልቻለም። ነጋሳ ደሳለኝ ዘገባ አለው ።
 
ነጋሳ ደሳለኝ 
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ