1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መተከል ዞን በኮማንድ ፖስት እንዲጠበቅ ተወሰነ

ሐሙስ፣ መስከረም 14 2013

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ ሲባል እስከ ህዳር  2013 ዓ.ም  የተወሰኑ ወረዳዎች  በኮማንድ ፖስት እንዲጠበቁ መወሰኑንን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

https://p.dw.com/p/3iwrF
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

የተደራጁ ቡድኖችንና ጥቃት የሚፈጽሙ ታጠቂዎች በመቆጣጠር ተጠያቂ ለማድረግ ነዉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ ሲባል እስከ ህዳር  2013 ዓ.ም  የተወሰኑ ወረዳዎች  በኮማንድ ፖስት እንዲጠበቁ መወሰኑንን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡ የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ መለሰ በየነ እንዳስታወቁት በአካባቢው ሰላምና ጸጥታ ለማስፈን  ለሶስት ወራት የወምበራ፣ቡሌን፣ዳንጉርና ጉባ ወረዳዎች በኮማንድ ፖስት የሚመሩ ናቸው፡፡ ከሰሞኑ በዞኑ ቡሌንና ወምበራ ወረዳዎች በታጣቂዎች በደረሰው ጥቃት በርካታ ሰዎች ከቤት ንብረቱ ተፈናቅለዋል፡፡ከ370 በላይ ተጠርጣዎችም በቁጥጥር ስር መዋቸው ተገልጸዋል፡፡  በሰው እና ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እስካሁን በመንግስት በኩል አልተገለጸም፡፡

 

 በመተከል ዞን ውስጥ ከሐምሌ 2011 ዓ፤ም አንስቶ የአካባቢውን የጸጥታ ችግርን ለመቅረፍ ሲባል የተወሰኑ ወረዳዎች ከዚህ በፊት በኮማንድ ፖስት ሲጠበቁ ቆይተዋል፡፡ከነሔሴ 23/2012 አንስቶ እስከ ጳጉሜ 2 2012 ዓ.ም በወምበራ ወረዳ እና ቡሌን ወረዳዎች ውስጥ በተለያዩ ቀናት በታጣቂዎች ከፍተኛ  ጉዳት መድረሱን ተከትሎ  ችግሩንም ለመፍታት ያስችላል የተባለ ለሶስት ወራት የሚቆይ ኮማንድ ፖስት  ስራ ጀምሯል፡፡ በመተከል ዞን ወምበራ ፣ቡሌን ጉባና ዳንጉር ወረዳዎች በኮማንድ ፖስት  እንደሚጠበቁ መወሰኑን የክልሉ ኮሙኑኬን ጉዳዩች ጽ/ቤት  ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ በስልክ አስረድተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ በታጣቂዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች የማቋቋም ተግባርም እንደሚከናወንና ከአካቢው ማህበረሰብ ጋር ምክክሮች ይደረጋሉ ብለዋል፡፡ አሁን በመተከል ዞን ስራ የጀመረው ኮማንድ ፖስትም ከሐምሌ 2011 ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ የተቋቋም ኮማንድ ፖስት ሲሆን ባለፈው በሚያዚያ ወር በአካባቢው ስራ ላይ የነበረው ኮማንድ ፖስት እቅዱ በመጠናቀቁና በአካባውም የጸጥታ ችግር ዳግም በመከሰቱ  በዞኑ ኮማንድ ፖስት እንገና ስራ መጀመሩን ኃላፊው አክለዋል፡፡

 

ያነጋርናቸው  በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ እና የቡሌን ወረዳ ነዋሪዎች ለ3ኛ ጊዜ በአካቢው ስራ የጀመረው ኮምድ ፖስት ሰላምና ጸጥታን በማስፈን የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀአቸው  ለመመስ፣ ወንጀለኞችም በማጋለጥ ለህግ በማቅረብ ፍትህን ማስፈን እነዳበት ያላቸውን አስተያየት ገልጸዋል፡፡ አንድ አንዶች ደግሞ ኮማንድ በአካቢው መታወጁ ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት የለንም ብለዋል፡፡በዚው አካባቢ በታጠቂዎች ደርሰዋል በተባለው ጉዳት የነዋሪውን ከቤት ንብረቱ መፈናቀልን በቀላሉ ለማስቆም በጊዜው የአካቢው ባለስልጣና  ሓላፊነታቸውን  ባለመወጣታቸው ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ ኮማንድ ፖስቱ ዘላቂ የሆነ ሰላም በማስፋን በአካባቢው የተደራጁ ቡድኖችንና ጥቃት የሚፈጽሙትን ታጠቂዎች በመቆጣጠር ተጠያቂ ማድረግ የመጀመሪያ ተግባሩ መሆን እንዳለበትም አክለዋል፡፡

 

በመተከል ዞን ቡሌንና ወምበራ ወረዳዎች  የደረሰውን ጥቃትን አስልመክቶም የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ እንዳስታወቁት ከሐምሌ 19 ወዲህ በወምበራ ቡሌንና ጉባ ወረዳዎች በተፈጠረው ጥቃች ሳቢያ ከ10ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በወምበራና ቡሌን ወረዳዎች ብቻ  ከ5ሺ በላይ ዜጎች መፈናቃላቸውን አብራርተዋል፡፡ በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡንና ወምበራ ወረዳዎች የደረሰውን ጥቃት የኢትዩጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያወገዘ ሲሆን ባለፉት ሁለት ወራት በነበሩት ጥቃቶች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር መረጃ ያሳያል፡፡ በጉባ ወረዳ ብቻ የነበሩት  አንድ ሺ ተፈናቃዩች ቁጥር አሁን ወደ አራት ሺ ማደጉን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ አብራተዋል፡፡

 

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ