ኤኮኖሚ
መቀሌ፣ የዋጋ ንረት
ዓርብ፣ ጥር 10 2011ማስታወቂያ
ትግራይ ርዕሠ ከተማ መቀሌ ዉስጥ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መምጣቱን የከተማይቱ ነዋሪዎችና ነጋዴዎች አስታወቁ።ሸማችና ሺያጮች እንደሚሉት በተለይ የእርሻ ምርትና የሥጋ እንስሳት ዋጋ አለቅጥ ጨምሯል።በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተዉ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና የኤርትራ ሸማቾች ወደ ኢትዮጵያ መግባት ለዋጋዉ ንረቱ እንደምክንያት ይጠቀሳሉ።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ እንደዘገበዉ አምና በዚሕ ወቅት 500 ብር ይሸጥ የነበረዉ አንድ ኩንታል በቆሎ ዘንድሮ 800 ብር ገብቷል።
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋለም ወልደየስ