1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መቀሌ በግጭት ማግሥት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 15 2013

በመቀሌ ስልክ፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የመድሐኒት መደብሮችና ታክሲዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል አገልግሎት እየሰጡ ነው። ነዳጅ ማደያዎች፣ ባንኮችና አብዛኞቹ ሱቆች ግን አሁንም ዝግ ናቸው። ፖሊስ ጣቢዎችና ፍርድ ቤቶችም ዝግ ናቸው። ለአንድ ወር ያሕል መዘገብ አቋርጦ የነበረዉ የመቀሌው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስላሴም ዛሬ ሥራ ጀምሯል

https://p.dw.com/p/3nC9s
Äthiopien Tigray | Hauptstadt Mekele
ምስል Edwin Remsberg/imago images

  መቀሌ በግጭት ማግሥት

ላለፉት ሁለት ወራት ግድም ተዋጊ ጄትና ሄሊኮብተርና የጦር አዉሮፕላኖች ሲያጉረመርሙበት የነበረዉ የመቀለ ሰማይ ዛሬ የመንገደኞች አዉሮፕላን ድምፅ ተሰምቶበታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ52 ቀናት በፊት አቋርጦት የነበረዉን የከና ወደ መቀሌ በረራ ዛሬ ጀምሯል። የትግራይ ርዕሠ-ከተማ አጠቃላይ እንቅስቃሴም እየተረጋጋ ነው። ስልክ፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የመድሐኒት መደብሮችና ታክሲዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል አገልግሎት እየሰጡ ነው። ሸቀጥም ወደ ከተማይቱ እየገባ ነው። ነዳጅ ማደያዎች፣ ባንኮችና አብዛኞቹ ሱቆች ግን አሁንም ዝግ ናቸው። ፖሊስ ጣቢዎችና ፍርድ ቤቶችም ዝግ ናቸው። ለአንድ ወር ያሕል መዘገብ አቋርጦ የነበረዉ የመቀሌው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስላሴም ዛሬ ሥራ ጀምሯል። በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ