1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መስቀል አደባባይና የጎዳና ኢፍጣር ዝግጅት ውዝግብ

ሰኞ፣ ግንቦት 2 2013

«ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መስቀል አደባባይን ጨምሮ በጎዳና ላይ የረመዳን የኢፍጣር ሥነ-ስርዓት ለማድረግ በእስልምና እምነት ተከታዮች ተይዞ የነበረው ፕሮግራም መሰረዙ አድሎአዊ እና ባይታዋርነትን የሚፈጥር ነው»ዑስታዝ አቡባከር አህመድ

https://p.dw.com/p/3tCsT
Äthiopien Meskel-Platz in Addis Abeba
ፎቶ፦ ከፋይልምስል DW/S. Muchie

«የአፍጥር መርሃግብሩ የተስተጓጎለው በጸጥታ ስጋት ነው» አዳነች አቤቤ

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መስቀል አደባባይን ጨምሮ በጎዳና ላይ የረመዳን የኢፍጣር ሥነ-ስርዓት ለማድረግ በእስልምና እምነት ተከታዮች ተይዞ የነበረው ፕሮግራም መሰረዙ አድሎአዊ እና ባይታዋርነትን የሚፈጥር ነው አሉ የሃይማኖቱ መምህር ዑስታዝ አቡባከር አህመድ፡፡

ጉዳዩም በቅርበት ሲመሩት የነበሩትና በመርሃግብሩ ዙሪያ ከመንግስት ባለስልጠናት ጋርም ተከታታ ውይይቶችን ሲያደርጉ የቆዩት ኡስታዝ አቡበከር ለዶይቼ ቬሌ እንዳሉት ትናንት ማምሻውን የፀጥታ አካላቱ ከምዕመኑ ጋር የፈጠሩት ግጭት በአመራር ክፍተት የተፈጠረ ብለውታል፡፡

በሂደቱ የተፈጠረውን አለመግባባት የፈጠሩ በህግም ሊጠየቁ እንደሚገባ የሚጠቁሙት ዑስታዝ አቡበከር በቀጣይ ሁለት ቀናትም የተሸለ ውጤት የሚያመጣ ያሉትን ውሳኔ ከመንግስት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ትናንት በመስቀል አደባባይ በተፈጠረው አለመግባባት ይቅርታን ጠይቀው፤ የኢፍጣር መርሃግብሩ የተስተጓጎለው በጸጥታ ስጋት ነው ብለዋል፡፡

 

ስዩም ጌቱ  

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ