1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብ

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 8 ከትዕይንት 1 እስከ 4)

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 14 2010

ወንጀል ተፋላሚዎቹ! አዲስ ተከታታይ ድራማ ጽሑፍ በፌስ ቡክ። በፈጣን የሴራ ፍሰት፥ በአጫጭር ትእይንቶች የተገነባው ድራማ በአይነቱ ለየት ያለ ነው። ይኽ የድራማ ጽሑፍ በዶይቸ ቬለ የአማርኛው ክፍል የፌስቡክ ገፅ የሚቀርብ ሲኾን፤ ለሽልማት የሚያበቃ ነው። ስለ ተሳትፎ እና ውድድሩ ፌስቡክ ገጻችን ላይ በዝርዝር ይገኛል።

https://p.dw.com/p/2j1km
09.2015 Crime Fighters MQ amharisch

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 8 ትዕይንት 1)

በስተመጨረሻ ሚ/ር ጂ ማን እንደሆነ ዐውቀናል። ቤቲ ደግሞ የማስፈራሪያ ዛቻ ትልክ እንደነበር የእምነት ቃሏን ሰጥታለች። ግን ጳውሎስን እሷ ካልገደለች ታዲያ ማን ሊሆን ይችላል? መርማሪ ከበደ ሁለቱን ሕገ-ወጥ አዳኞች ምርመራ ክፍል ውስጥ እያነጋገረ ነው።

«ሁለታችሁም ከተባበራችሁን በቅጣት ማቅለያነት ሊረዳችሁ ይችላል፡፡ መቼም እስር ቤት ከመበስበስ ይሻላል።»

«ወደ ጳዉሎስ ቤት የሄድነለአለቃችን አንድ ቪዲዮ ለማምጣት ነበር።  ነገር ግን ብናስፈራራውም ጳዉሎስ አልሰጥም ብሎ ከእሱ ጋር ግብግብ ገጠመ። ከዛ እንዴት እንደሆነ እንጃ ሞተ።»

«አንተ ደደብ! ምን እንደሚገጥምህ ሳታውቅ ትዘላብዳለኽ?!»

«አለቃችኹ ማን ነው?»

«እሱን እንኳን ሰዎቹ አደገኛና ኃይለኞች ስለሆኑ ልነግርህ አልችልም 

«መልካም! በእኔ ግምት ግን አለቃችሁ ሚስተር ነው እና ሚስተር ማለት ደግሞ ዶክተር ሰናይት ነች፡፡ ኖችን ታድን የተቀረጸችውን ቪዲዮ ተመልክተነል፡፡ ሁለታችሁም ደግሞ እዛው ከስዋ ነበራችሁዶክተር ሰናይትም እዚሁ እስር ቤት ነው የምትገኘው።»

«አዎ…አለቃችን  እሷ ናት፡፡ አለቃችን እሷ ናት።»

«ይኽን ፍርድ ቤት ቀርበህ ለመመስከር ፍቃደኛ ነህ?»

«እእእይህን ካደረግኹ ቅጣት ይቀልልኛል?»

«እንደዛ የመኾን ዕድሉ በጣም ሰፊ ነው።»

«እንደዛማ ከኾነ ፍቃደኛ ነኝ!»

በእርግጥ ሁለቱ ሕገ-ወጥ አዳኞች እውነቱን አፍረጥርጠው ይናገሩ ይኾን?

***

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 8 ትዕይንት 2)

በመጨረሻም እውነቱ ገሐድ ወጣ! እነዚህን ሁሉ ማስረጃዎችና ምስክሮች በመያዝ ዓለሙ እና ከበደ ለሚስተር ጂ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች ይዘዉ ወደ ሌላኛው የምርመራ ክፍል ገብተዋል።

«/ ሰናይት ነገሮችን በጥሞና የምታስቢበት በቂ ጊዜ እንዳገኘሽ  ተስፋ አደርጋለሁ ።»

«ነግሬሃለኹ፤ ከጠበቃዬ ጋር ሳልማከር ምንም መልስ አልሰጥኽም።»

«ዝምታሽ ከምንም አያድንሽም! እራስሽ የቀጠርሻቸው ሕገ ወጥዳኞቹ የሚያውቁትን ተናዘዋል። ለአንቺ ተቀጥረው ሕገ-ወጥ አደን እንደፈፀሙ ቃላቸውን ሰጥተዋል። እናም ጳዉሎስን ንዲገድሉ  ያዘዝሻቸው አንቺ ነሽ!»

«ም?! እነዚያ ደደቦች

«/ መቼም ይሄ ደግሞአንቺ ሕገ-ወጥ አዳኝ ብቻ አለመሆንሽን ነው የሚያሳየው። ስለዚህ የግድያውን ወንጀል ማቀነባበር ሴራም ተጨማሪ ክስ እንመሰርትብሻለን!»

«እለዚህ እንኳን ምንም ተጨባች ማስረጃ የለህም

«አለኝ እንጂ! የራስሽ ቅጥረኛ ሊመሰክርብሽ ተስማምቷል፡፡ ሚስተር አዝናለሁ! የረጅም ዘመን እስር ይጠብቅሻል

«ወይኔ ልጅት!»

«እኔ ግንይሄን ሁሉ ነገር ለምን እንደፈጸምሽው ነው ግራ የገባኝ! ምን ጎድሎብሽ ነው አሁን…? የተስተካከለና ስኬታማ ሕይወት አለሽ! ክብር፣ ዝና፣ ሀብት ነበረሽ!እኔ አልገባኝም»

«ከንቱ ጊዜ! ለዓመታት ማሰንኩ፣ ኳተንኩ፣ ለፋኹ። አንዳች ጠብ የሚል ነገር የለም! መጨረሻም ያው ገንዘብ አሸነፈኝ።»

«እናም የዱር አራዊት ተሟጋችነቱ ሥራሽ ጥሩ ሽፋን ስለሆነሽ እሱንም ቀጠልሽበት

«አዎን።»

«እንግዲህ የእኛ ሥራ ተጠናቋል። አንቺም ቀሪ እድሜሽን በወህኒ ቤት ታሳልፊያለሽ።»

የዶ/ር ሰናትይት ነገር «ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ ዓልሞ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ!» እንደተባለው ኾኗል። የቤቲ ዕጣ ፈንታም ከዚህ የተለየ የሚሆን አይመስልም። 

***

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 8 ትዕይንት 3)

የወንጀል ምርመራ ክፍሉ እጅግ ቀዝቅዟል።  መርማሪ ዓለሙ ወደ ምርመራ ክፍሉ ይገባል። ባልደረባው መርማሪ ከበደ እጁን ለማሞቅ እያሻሸ ነው።

«ኧረግ ኧረግ ኧረግ፤ እንዴት ይቀዘቅዛል ባክህ» 

«በጣም እንጂ! ይሄኔ እነዛ የእስር ቤት የብረት ፍርግርጎች በረዶ ሠርተዋል!»

«ባክህ፤ ከቅንጦት ሕይወት ለመጡት ለእነ / ሰናይት አይነቶቹ ጥሩ ለውጥ ይሆናቸዋል፡፡»

«እንግዲህ ትቻለው»

«ያው በድምሩ  40 ዓመት እስራቷን ጠጥታ አረፈችው አይደል?»

«እንግዲህ ለፓውሎስና ለገደለቻቸው እንስሳት ነፍስ ጸሎት ስታደርስ ትኑር።»

«ያማ ለጽድቅ ይሆናት ነበር። ይልቅ ባክህ አለቃዬ ደሞ ሚ/ር ጆርጅ ጋር ካልደወልክ ብሎ አንቆ ይዞኛል። በል ቢሮዬ ልመሽግና በሚ/ር ጆርጅ እና የወንጀል መረቡ ላይ ክትትሌን ልጀምር።»

«እኔም ተወጥሬልሀለሁ  ከቤ፤ ከአንድ ሰአት በኋላ ችሎት ፊት ቀርቤ በቤቲ ላይ የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ። አቃቤ ሕጉ እስከ 20 ዓመት ሊፈረድባት ይችላል።»

«እንዴ ዓለሙ! ለገንዘብ ሲባል ለተደረገ የማስፈራራት ወንጀል ትንሽ አልበዛም?»

«በፍጹም! አስፈራርቶ ገንዘብ መቀበል በራሱ ከባድ ወንጀል ነው! በተጨማሪም ደግሞ በዚሁ ምክንያት የሌላ ሰው ሕይወት አደጋ ላይ መውደቁ የከፋ ወንጀል ያደርገዋል። እሷ በተዘዋዋሪም ቢሆን ለጳዉሎስ ሞት ተጠያቂ ነች ስለዚህ ነው ቅጣቱ ሊከብድባት የሚችለው።»

«ገና የሕገ-ወጥ አዳኞቹም ቀጠሮ ነገ ነው።» 

«በተለይ ጳዉሎስ ገዳይ ላይ፤ ከሕገወጥ አደኑ ጋር ተዳምሮ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ሳይፈርዱበት አይቀርም። ጆንም ከሕገወጥ አደኑ ወንጀል ብቻ እስከ 50 ዓመት እስራት ይጠብቀዋል።»

«በል እንግዲህ ወንድሜ መልካም ሥራ ይሁንልህ!»

አሜን!»

የግድያው ወንጀ።ል ዋነኛ ተጠርጣሪ የነበረችው ሉሲ፤ ማለትም የሟቹ የፓውሎስ ሚስት፤ ከወንጀሉ ነጻ ሆናለች። የባሏ እህት ሙናም ከሐዘኗ ስታጽናናት ከርማለች። እነዚህ ሁለት ሴቶችስ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ይሆኑ?

***

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 8 ትዕይንት 4)

በሰዎች በተጨናነቀው አዳርሽ ውስጥ ሉሲ እና የጳውሎስ እህት ሙና ከፊት ለፊት ቆመዋል። ሙና ንግግር ለማድረግ ጉሮሮዋን ስታጸዳ በአዳራሹ ውስጥ የነበረው ጫጫታ በዝግታ መክሰም ይጀምራል።

«ዛሬ እዚህ የተሰበስብነው በሁለት የተቀደሱ ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያው በዘግናኝ ሁኔታ የተገደለዉ  ወንድሜ የሉሲ ባል ጳውሎስን ለማሰብ ነው።»

«መቼም ሁላችሁም በግፍ የተገደለው ባለቤቴ ጳዉሎስ ለእንስሳት የነበረውን ፍቅር ታውቃላችሁ።»

ታዳሚያኑ የድጋፍ ድምፅ ያሰማሉ። ሉሲ ንግግሯን ትቀጥላለች።

«ስለዚህ ዛሬ ለሱ መታሰቢያ የሚሆነውን ይህን የዱር እንስሳት ጥበቃ በይፋ መርቀን እንከፍታለን!»

ታዳሚያኑ አሁንም በደስታ የድጋፍ ድምፃቸውን ያሰማሉ። ሙና ስለ ማኅበሩ ዓላማ ታብራራለች።

«የዚህ ማኅበር ዋነኛ ዓላማዎች በዱር እንስሳት አስፈላጊነት ላይ ለኅብረተሰባችን ትምህርት መስጠት፤ በሰዎችና በዱር እንስሳት መካከል የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት፤ ብሎም ሕገ-ወጥ አደን የሚፈጸምባቸውን ዋና ዋና ስፍራዎች ለይቶ ማወቅ ይሆናል።»

ጎላ ያለ ድጋፍ ከታዳሚያኑ ይሰማል። ሉሲ ትቀጥላለች።

«እንደ ዶ/ ሰናይት የመሰሉ ከሃዲዎች ዱር እንስሳት ጥበቃ ሽፋ ኪሳቸውን አያደልቡም

«ፈጽሞ! ፈጽሞ!»

«ሁላችንም ተባብረን የተሻለ ነገር እንራለን»

የድጋፍ ድምፁ ይጎላል። ሉሲ በዝግታ ትናገራለች።

«ስለዚህ አሁን ሁላችንም ጳዉሎስን ኅሊናችን  እያሰብን  ለእሱ መታሰቢያነት የተቋቋመውን ይህን የዱር እንስሳት ጥበቃ ማኅበር ምስረታን በይፋ እናብስር

በአዳራሹ ሞቅ ያለ ጭበጨባና የድጋፍ ድምፅ ያስተጋባል።

-ተፈጸመ-

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 1 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 2 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 3 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 4 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 5 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 6 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 7 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

ጀምስ ሙሃንዶ

ማንተጋፍቶት ስለሺ