1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕወሓትና የዶክተር አረጋዊ በርሔ አስተያየት

ሰኞ፣ ኅዳር 21 2013

የሕወሓት መስራች፣ የቀድሞ መሪና የሕዳሴ ግድብ የህዝብ ድጋፍ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር አረጋዊ በርሔ እንደሚሉት  የፌደራዊ መንግስቱን ለወታደራዊ ርምጃ የገፋፋዉ የሕወሓት መሪዎች ሕግ ከመጣስ ባለፍ ለሽምግልና፣ ለድርድር፣ለአዋቂዎች ምክር ዝክርም እንቢኝ ማለታቸዉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3m2hQ
Äthiopien Tigrean Alliance for National Democracy | Aregawi Berhe & Asgede Gebreselassie
ምስል DW/S. Muchie

«አምባገነኖች የሚመሩት ድርጅት መሪዎቹ ሲጠፉ ይጠፋል።» ዶር አረጋዊ በርሔ

የሕወሓት መስራች፣ የቀድሞ መሪና የሕዳሴ ግድብ የህዝብ ድጋፍ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር አረጋዊ በርሔ እንደሚሉት  የፌደራዊ መንግስቱን ለወታደራዊ ርምጃ የገፋፋዉ የሕወሓት መሪዎች ሕግ ከመጣስ ባለፍ ለሽምግልና፣ ለድርድር፣ለአዋቂዎች ምክር ዝክርም እንቢኝ ማለታቸዉ ነዉ።ዶክተር አረጋዊ አክለዉ እንዳሉት ሕወሓትን የሽምቅ ተዋጊ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ የሚመሩት ኃይላት ከአንድነት ይልቅ መገንጠልን፣ከዴሞክራሲያዊነት ይልቅ አምባገነናዊነትን፣ ከድርድር ይበልጥ በኃይል መታበይን የሚያስቀድሙ ናቸዉ።የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ መሪዎች የሽምቅ ዉጊያ መጀመራቸዉን አስታዉቀዋል።ይሁንና ዶክተር አረጋዊ እንደሚሉት የሕወሓት መሪዎች እንደ ተራ ሽፍታ ላጭር ጊዜ ጉዳት ከማድረስ አልፈዉ እንደ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን ለመቀጠል የዘመኑ ቴክኖሎጂ አይፈቅድላቸዉም፤ ከሁሉም በላይ የሕዝብ ድጋፍ ስለሌላቸዉ ለረጅም ጊዜ መዋጋት አይችሉም።

ነጋሽ መሐመድ