1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕወሓት አፋር ውስጥ ይዞታዎችን መቆጣጠሩ ተገለጠ

ማክሰኞ፣ ጥር 17 2014

ሰሜናዊ የአፋር ክልል አካባቢ የሆኑትን በርሃሌን እና መጋሌን ሕወሓት እንደ አዲስ በከፈተው ጥቃት ምክንያት በቁጥጥሩ ሥራ እንዳደረጋቸው የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገለፀ።የክልሉ መንግሥት እንዳለው የፌዴራል መንግሥት ለሰላም ባለው ፍላጎት ምክንያት በአካባቢዎቹ የመከላከያ ሠራዊት የለም።

https://p.dw.com/p/463Gy
TABLEAU | Internationaler Tag gegen Kinderarbeit 2021 | Äthiopien
ምስል Michael Runkel/ImageBroker/picture alliance

ሕወሓት በርሃሌንና መጋሌን መቆጣጠሩ ተነግሯል

ሰሜናዊ የአፋር ክልል አካባቢ የሆኑትን በርሃሌን እና መጋሌን ሕወሓት እንደ አዲስ በከፈተው ጥቃት ምክንያት በቁጥጥሩ ሥራ እንዳደረጋቸው የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገለፀ።የክልሉ መንግሥት እንዳለው የፌዴራል መንግሥት ለሰላም ባለው ፍላጎት ምክንያት በአካባቢዎቹ የመከላከያ ሠራዊት የለም። ሕወሓት ከዚህ በፊት በአፋር እና አማራ ክልሎች ገብቶ እያለ ያደርግ የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አሁንም በንፁሃን አርብቶ አደሮች ላይ እየፈፀመ መሆኑንም ክልሉ ተናግራል።የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አሕመድ በአፋር ክልል ዞን ሁለት ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሦስት ወረዳዎች ላይ ከሳምንት በፊት ጀምሮ በሕወሓት ታጣቂዎች ጥቃት ሲደርስ ሰንብቷል ብለዋል። ሕወሓት አብአላን ተቆጣጠረ ማለት የአዲስ አበባ ጅቡቲን አውራ ጎዳናን ለመያዝ አመቺ ስለሚሆንለት መንግሥት ይህንን እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብም አፋር እየታገለ ያለው ለመላው አገሪቱ ደህንነት መሆኑን በመገንዘብ ሞቱን ሞቴ ሊለው ይገባል ብለዋል። ሕወሓት ከዚህ በፊት በአፋር ክልል አራት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 21 ወረዳዎች ላይ በመግባት መጠነ ሰፊ ጉዳት ማድረሱን የክልሉ መንግሥት ተናግራል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ