1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ሕወሓት በጉልበት ወስዷቸዉ የነበሩ አካባቢዎች አይመለሱም» የአማራ ክልል

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 6 2013

የአማራ ክልል የመንግስት ባለፉት ዓመታት በህወሓት በጉልበት የተወሰዱ የአማራ አካባቢዎች በመስዋዕትነት የመጡ አካባቢዎች ጉዳይ ላይ ጊዜ ማጥፋት ተገቢ አይደለምም ሲል ገለፀ። የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር እንደተናገሩት አካባቢዎቹ የክልሉ መንግሥት አስተዳዳሪዎችን መድቦ የሚተዳደሩ ናቸው ወደኋላ የሚመለስ ነገር የለም ሲሉ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3wQVj
Äthiopien Gizachew Muluneh General Director Amhara Communication Office Bahar Dar
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

«ህወሓት በጉልበት ወስዷቸዉ የነበሩ አካባቢዎች አይመለሱም» የአማራ ክልል መንግሥት

«ወሓት በጉልበት ወስዶቸዉ የነበሩ አካባቢዎች አይመለሱም» የአማራ ክልል መንግሥት
የአማራ ክልል የመንግስት ባለፉት ዓመታት በህወሓት በጉልበት የተወሰዱ የአማራ አካባቢዎች በመስዋዕትነት የመጡ አካባቢዎች ጉዳይ ላይ ጊዜ ማጥፋት ተገቢ አይደለምም ሲል ገለፀ። የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በተለይ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት አካባቢዎቹ የክልሉ መንግሥት አስተዳዳሪዎችን መድቦ የሚተዳደሩ ናቸው ወደኋላ የሚመለስ ነገር የለም ሲሉ ተናግረዋል። ህወሓት ደቡባዊ ትግራይ ከምትላቸው አካባቢዎች መካከል አንዳንዶቹን መቆጣጠሯን የተለያዩ የዉጭ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነዉ። ከአላማጣ ቅርብ እርቀት ከምትገኘው ቆቦ ከተማ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ አንድ የዓይን እማኝ ከትናንት ጀምሮ በርከት ያሉ ሰዎች አላማጣን እየለቀቁ ወደ ቆቦ መግባታቸውን ተናግረዋል። የባህር ዳሩ ወኪላችን ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል። 

ዓለምነዉ መኮንን

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ