1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ልደቱ አያሌው በሕመም ሳቢያ ከፖለቲካ መገለላቸውን አስታወቁ

ረቡዕ፣ መጋቢት 1 2013

ለረጅም ዓመታት በተቃውሞ የፖለቲካ ጎራ ተሳታፊነታቸውና አማራጭ ሀሳብ አፍላቂነታቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ለጊዜው ከፖለቲካ ትግል መድረክ መውጣታቸውን ገለፁ። ፓለቲከኛው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት እንደ እሳቸው አባባል ከፍተኛ የልብ ታማሚ ሆነው ሳለ መንግሥት ውጭ ሄደው እንዳይታከሙ ስለከለከላቸው በህይወት ለመሰንበት ነው።

https://p.dw.com/p/3qRIV
Äthiopien Pressekonferenz EDP in Addis Abeba
ምስል DW/G. Tedla

ልደቱ አያሌው በሕመም ሳቢያ ከፖለቲካ መገለላቸውን አስታወቁ

ለረጅም ዓመታት በተቃውሞ የፖለቲካ ጎራ ተሳታፊነታቸውና አማራጭ ሀሳብ አፍላቂነታቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ለጊዜው ከፖለቲካ ትግል መድረክ መውጣታቸውን ገለፁ።
ፓለቲከኛው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት እንደ እሳቸው አባባል ከፍተኛ የልብ ታማሚ ሆነው ሳለ መንግሥት ውጭ ሄደው እንዳይታከሙ ስለከለከላቸው በህይወት ለመሰንበት ነው።
አቶ ልደቱ ይህንን ውሳኔ ባሳወቁበት ግልፅ ደብዳቤያቸው ኢትዮጵያ አሁን ከፍተኛ የህልውና አደጋ ውስጥ እንደምትገኝና ከጎረቤት አገራት የተቃጣባትን ግልፅ ወረራ ለመቀልበስ የሚያስችል ወኔና አቅም ያጣች ደካማ ሀገር ሆናለች ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ