1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ልዩ ቃለ-ምልልስ ከአምባሳደር ኩማ ደመቅሳ ጋር

እሑድ፣ ጥቅምት 18 2011

በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ኩማ ደመቅሳ በርሊን ላይ ከወኪላችን ጋር ባደረጉት የመጀመሪያው ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጀርመን አገር ስለሚያደርጉት ጉብኝት ማብራሪያ ሰጥተዋል። አምባሳደሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በአሜሪካ ካደረጉት ለየት ያለ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

https://p.dw.com/p/37HWu
München Konferenz Ethiopia - Africa's new business destination
ምስል DW/S.M. Sileshi

ልዩ ቃለ-ምልልስ ከአምባሳደር ኩማ ደመቅሳ ጋር

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከነገ ጀምሮ በፈረንሳይ እና ጀርመን ጉብኝት ያደርጋሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጀርመን በሚኖራቸው ቆይታ ከመራሔተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር የሚናኙ ሲሆን በአፍሪካ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ላይ በሚያተኩር ስብሰባ ላይም ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በመጪው ረቡዕ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ደግሞ ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በጀርመኗ ፍራንክፈርት ከተማ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ዙሪያ ከDW ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ በፍራንክፈርቱ ዝግጅት ላይ 20 ሺህ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። በጊዜ ጥበት ምክንያት ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ እንዳደረጉት ሌሎች ስብሰባዎችን ከኢትዮጵያውያን ጋር እንደማያካሄዱ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳን ከወጣትነታቸው ጊዜ ጀምሮ እንደሚያውቋቸው የሚናገሩት አምባሳደር ኩማ ያንን ጊዜ በቃለ ምልልሳቸው ላይ መለስ ብለው አስታውሰዋል።

አቶ ለማም ሆነ ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን እንዲመጡ ምክንያት የሆነውን ህዝባዊ አመጽ እና እርሱን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ እና የቀድሞው ኦህዴድ አካሂደዋቸው ስለነበሯቸው ተከታታይ ስብሰባዎችም የሚሉት አለ። በኢትዮጵያ አሁን በየቦታው ስለሚታየው ግጭት እና አለመረጋጋት ተጠይቀውም ምላሽ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ ከበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።  

ይልማ ኃይለሚካኤል 

ተስፋለም ወልደየስ