1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርት

ሊስትሮዋ የኮሌጅ ተማሪ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 16 2013

ሊስትሮዋ የኮሌጅ ተማሪ

https://p.dw.com/p/3mxvE

ጥበቢቱ ጥላሁን በሐዋሳ ከተማ በሴቶች ብዙም ባልተለመደው የሥራ መስክ ፣ በሊስትሮ ወይም ጫማ በመጥረግ ሥራ ትተታደራለች። ሥራውን የጀመረችው ሆን ብላ በከተማው « ሴት የማትሰራው ሥራ ምንድን ነው?» ብላ ነው። መጀመሪያ ላይ ሥራው ፈታኝ ቢሆንባትም በደንበኞቿ ርዳታ ሥራውን ወዲያው መልመዷን ትናገራለች። አሁን በዚህ ሥራ በምታገኘው ገንዘብ ራሷን ብቻ ሳይሆን የምታስተዳድረው ጎን ለጎን ኮሌጄም ትማራለች። ለሌሎች ወጣት ሴቶች የምትለው « የሥራ ትንሽ የለውም» ነው። #GirlZOffMute.

ዘገባ: ሊሻን ዳኜ

ቪዲዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ