1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለዐማራ ክልል ተፈናቃዮች የሚደረግ ድጋፍ

እሑድ፣ ጥቅምት 7 2014

ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው ጦርነት ምክንያት በዐማራ ክልል ተፈናቅለው የአስቸኳይ ዕርዳታና ህክምና የሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ እየቀረበ ነው:

https://p.dw.com/p/41n1A
Äthiopien Dr Tizazu Asrat
ምስል T. Hailu/DW

ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው ጦርነት ምክንያት በዐማራ ክልል ተፈናቅለው የአስቸኳይ ዕርዳታና ህክምና የሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ እየቀረበ ነው። በዐማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ግብረሃይል የተቋቋመው የህክምና ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ትዕዛዙ አስረስ ለዶይቸ ቬለ እንደገለፁት ለተፈናቃዮቹ የሕክምና ዕርዳታ ለመስጠት የሚያስፈልጉ የህክምና መሣሪያዎች የመድኃኒት፣ የምግብ የመጠጥ ውኃና የአልባሳት አቅርቦት ችግር አለባቸው::

በሌላ በኩል በአሜሪካ የአማራ አስቸኳይ ጊዜ ገንዘብ ማሰባሰብ ግብረሃይል አስተባባሪ አቶ ተመስገን መንግስቱ ከትናንት ቅዳሜ አንስቶ ለተፈናቃዮቹ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ የሚያስችል ዘመቻ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። 

ታሪኩ ኃይሉ

ልደት አበበ