1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለዋሽንግተኑ ቀዉስ ትራምፕ ተጠያቂ ናቸዉ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 29 2013

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኅዳር ወር ጀምሮ በምርጫ ተሸናፊ መሆናቸዉን አለመቀበላቸዉ አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛልም። በትናንቱ ክስተትም ሽንፈታቸዉን አልተቀበሉም።» 

https://p.dw.com/p/3nelq
Deutschland Berlin | Angela Merkel, Bundeskanzlerin
ምስል Kay Nietfeld/dpa/picture alliance

የፕሬዚዳንት ትራምፕ ደጋፊዎች ዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት «ካፒቶልን»ን ኃይል በቀላቀለ ሁኔታ ጥሰዉ መግባታቸዉ የዓለም መንግሥታት እያወገዙት ነዉ። በዋሽንገግተኑ ክስተት ድንጋጤ እና ሃዘን እንደተሰማቸዉ የገለፁት የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ለነበረዉ ነገር ሁሉ ፕሬዚዳንት ትራምፕን ተጠያቂ አድርገዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ኅዳር ላይ በተካሄደዉ ምርጫ መሸነፋቸዉን አሁንም አለመቀበላቸዉ አሳዛኝ ነዉ፤ ይህ ባለማድረጋቸዉም ለዉዝግብና ግጭት ግብዣን ፈጥረዋል ሲሉ ሜርክል አክለዋል። የዴሞክራሲዉ ዋና መሰረት ከምርጫ በኅላ አሸናፊ እና ተሸናፊ መኖሩ ነዉ ሲሉ ሜርክል አክለዋል።  
« መሰረት ያለዉ የዴሞክራሲ ርምጃ ከምርቻ በኋላ አሸናፊ እና ተሸናፊ መኖሩ ነዉ። ሁለቱም ወገኖች ዴሞክራሲ አሸናፊ ሆኖ እንዲቀጥል በየፊናቸዉ ኃላፊነታቸዉን ይወጣሉ። በዚም ምክንያት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኅዳር ወር ጀምሮ በምርጫ ተሸናፊ መሆናቸዉን አለመቀበላቸዉ አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛልም። በትናንቱ ክስተትም ሽንፈታቸዉን አልተቀበሉም።» 
በአሜሪካ ከበጥባጦች ይልቅ የዴሞክራሲ መሰረት ጠንካራ መሆኑን ሜርክል ተናግረዋል። የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በበኩላቸዉ ዉሸት እና ጥላቻ ፀረ ዴሞክራሲ ናቸዉ ብለዋል። 
«ካፒቶል ላይ የሆነዉን ምስል እያየን ነዉ።ሌላ ቅርፅና ገፅታ ቢኖረዉም፣ ባለፈዉ ዓመት የፀረ-ዴሞክራሲ ኃይላት የራይሽታግ (የጀርመን ምክር ቤት) ሕንፃ ደረጃዎችን የመያዛቸዉን ምስል  አንረሳዉም።በዚሕም ምክንያት ዛሬ ለሁላችንም ይሕን መልዕክት አስተላልፋለሁ።ጥላቻና የጥላቻ ቅስቀሳ ዴሞክራሲን ላደጋ ያጋልጣሉ።ዉሸት ዴሞክራሲን ይጎዳል።ረብሻ ዴሞክራሲን ያዉካል።

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ