1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአማራ ተፈናቃዮች ርዳታ ተሰጠ

ረቡዕ፣ ግንቦት 14 2011

የክልሉ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና መስሪያ ቤት እንዳስታወቀዉ ለተፈናቃዮቹ መርጃ ከ330 ሚሊዮን በላይ ብር ከተለያዩ ለጋሾች ተረክቧል

https://p.dw.com/p/3IuvE
Äthiopien | Übergabe von Hilfsgeldern an die Vertriebenen der Region Amhara
ምስል DW/A. Mekonnen

ለአማራ ተፈናቃዮች ርዳታ ተሰጠ

                                 
በአማራ ክልል በተከሰቱ ግጭቶችና ከሌሎች ክልሎች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል የሠፈሩ የአካባቢዉ ተወላጆችን መልሶ ለማቋቋም የሚሰጠዉ ርዳታ እንደቀጠለ ነዉ።የክልሉ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና መስሪያ ቤት እንዳስታወቀዉ ለተፈናቃዮቹ መርጃ ከ330 ሚሊዮን በላይ ብር ከተለያዩ ለጋሾች ተረክቧል።በአማራ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ከ107 ሺሕ በላይ የክልሉ ነዋሪዎች በተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለዋል።ከተፈናቃዮቹ መካከል 36 ሺሕ የሚሆኑት ሰሞኑን ወደቀየቻዉ መመለሳቸዉ ተዘግቧል።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋአለም ወልደየስ