1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለተፈናቀሉ ወገኖች የኢትዮጵያውያን ርዳታ

ረቡዕ፣ ግንቦት 7 2011

ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን ሀገር ውስጥ የተከሰተው የመፈናቀል ችግር በቀላሉ የማይታይና ከፍተኛ አደጋ ያስከተለ መሆን አመለከተ። በጌዲኦ እና በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰበውን 37 ሚሊየን ብር ዛሬ ያስረከበው ድርጅቱ፤ ዜጎች ለምን ይፈናቀላሉ?

https://p.dw.com/p/3IYSd
Global Alliance-Spende für vertriebene Äthiopier
ምስል DW/S. Muchie

37 ሚሊየን ብር ለተፈናቀሉ መርጃ ሰጥቷል

 መፈናቀል እስከመቼ ይቀጥላል የሚለው በአፋጣኘን መልስ ሊያገኝ የሚገባው ጉዳይ ነው ሲል አሳስቧል። ዜጎች «ይህ የኔ ሃገር ነው» የሚለው እምነታቸው እንዲመለስ እና መሰል ችግሮች እንዲቀረፉም በቀጣይ የእርቅ ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ ማቀዱን  የትብብሩ ፕሬዝዳንት  ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያዊያን መብታቸው እንዲከበር ከፍተኛ ሥራ ሲያከናውን እንደቆየ በመጥቀስ በተለይም በመቶ ስዎች የተፈናቀሉበት የጌዴዎ እና የጉጅ ዞኖች ግጭት ባደረሰውን ጥፋት ለተጎዱት ከመላው ዓለም 18 ሽ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን  ከ31.4 ሚሊዮን ብር በላይ በማዋጣት ቤቶች እንዲገነቡ ፤ መልሰው ወደነበሩበት እንዲመለሱ እና የመቋቋሚያ ገንዘብ እንዲያገኙ ለማድረግ ሙሉ ገንዘቡን ለወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ዛሬ አስረክቧል። በዚህም ወደ 1710 ቤቶች ይገነባሉ ተብሏል። ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የተመረጠበት ምክንያትም በስፍራው ሰፊ የሰው ኃይል ያላቸው መሆኑ፤ ልምዳቸውና ከምንም በላይ የሥራ ማስኬጃውን ወደ 5.7 ሚሊዮን ብር ራሱ ድርጅቱ ለመሸፈን ሙሉ በሙሉ በመስማማቱ መሆኑ ተገልጽዋል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን ከዚህ በተጨማሪም በጎንደር በተቀሰቀሰው ግጭት መፈናቀልና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በዚሁ ዕለት የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

Global Alliance-Spende für vertriebene Äthiopier
ምስል DW/S. Muchie

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ