1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለቦይንግ አደጋ ሰለባ ቤተሰቦች ካሳ

ሰኞ፣ የካቲት 30 2012

ባለፈው ዓመት በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሰለቦች አንደኛ ዓመት መታሰብያ ነገ እንደሚከናወን ተገለፀ። በአሜሪካ የሚገኝ ለተጎዱት ጥብቅና የሚቆም የህግ ተቋም ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጠው መግለጫ ቦይንግ ለአደጋው ሰለባ ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ግፊት እያደረኩ ነው ብሏል።

https://p.dw.com/p/3Z6r1
Äthiopien Addis Abeba | Treffen von Anwälten wegen Kompensationen für die Opfer des Flugzeugunglücks der verunglückten Ethiopian Airline 737 Max 8
ምስል DW/S. Muchie

ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ያደረገዉ በአደጋ ለተጎዱ ጥብቅና የሚቆም የህግ ተቋም

ባለፈው ዓመት በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሰለቦች አንደኛ ዓመት መታሰብያ ነገ እንደሚከናወን ተገለፀ። መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አድርጎ በዚህና ሌሎች አደጋዎች ለተጎዱት ጥብቅና የሚቆም የህግ ተቋም ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጠው መግለጫ ቦይንግ ለአደጋው ሰለባ ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ግፊት እያደረኩ ነው ብሏል። በዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት እየታየ ያለው ጉዳይ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰም ለደንበኞቼ በየጊዜው መረጃ አደርሳለሁ ብሏል ድርጅቱ። ከደቡብ አፍሪካ የመጣውና በአደጋው ሴት ልጁን ያጣው ተጎጂ ቤተሰቦች ሃዘናቸውን ተሰባስበው በጋራ መታደማቸው እንዳስደሰተው ገልጾ፣ ዓለም ለሰው ልጅ ቅድሚ እንድትሰጥ ጠይቋል። ባለፈው ዓመት በደረሰው አደጋ የ 33 አገራት 157 ሰዎች ሙሉ አልቀዋል።


ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ