ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሌላ አማራጭ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ በመንግሥት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚታየውን የተማሪዎች የመቀበል የአቅም ውስንነት ለመፍታት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሙያ ቀስመው የሚመረቁበትን አማራጭ አቅጣጫ ሊከረል እንደሚችል የትምሕርት ሚኒስቴር አስታወቀ። 12ኛ ክፍል ደርሰው የከፍተኛ ትምሕርት ዕድል ማግኘት የማይችሉ ተማሪዎች አማራጭ የሙያ ስልጠና አግኝተው ሥራ እንዲፈጥሩ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ተናግረዋል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሚኒስትር ዲኤታውን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ