1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለተኛዉ ዙር የኮቪድ 19ኝ ሥጋት በጀርመን 

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 28 2012

የጀርመን የፌደራልና የክፈለ-ሐገራት የጤና ባለስልጣናት ሁለተኛዉ ዙር የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን ለመከላከል እስካሁን ከተወሰዱት በተጨማሪ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነዉ።ባለስልጣናቱ ለጉብኝትና ለእረፍት  ዉጪ ሐገር ሰንብተዉ የሚመለሱ የጀርመን ዜጎች እና ነዋሪዎች በየሚደርሱበት አዉሮፕላን ማረፊያ ምርመራ እንዲደረግላቸዉ ወስነዋል።

https://p.dw.com/p/3gPNk
DEutschland | Schulbeginn in Mecklenburg-Vorpommern
ምስል picture-alliance/dpa/J. Büttner

መምሕራን፣ ተማሪዎችና ሌሎች ሠራተኞች  የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እያሳሰቡ ነዉ


የጀርመን የፌደራልና የክፈለ-ሐገራት የጤና ባለስልጣናት ሁለተኛዉ ዙር የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን ለመከላከል እስካሁን ከተወሰዱት በተጨማሪ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነዉ። ባለስልጣናቱ ለጉብኝትና ለእረፍት  ዉጪ ሐገር ሰንብተዉ የሚመለሱ የጀርመን ዜጎች እና ነዋሪዎች በየሚደርሱበት አዉሮፕላን ማረፊያ ምርመራ እንዲደረግላቸዉ ወስነዋል። ከበጋዉ ዕረፍት  በኋላ ትምሕርት ቤቶች የሚከፍትበት ወቅት በመሆኑም መምሕራን፣ ተማሪዎችና ሌሎች ሠራተኞች  የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እያሳሰቡ ነዉ።ይሁንና መንግስት የሚወስዳቸዉን እርምጃዎች በመቃወም የአደባባይ ሰልፍ የሚያደርጉም አሉ። 

DEutschland | Schulbeginn in Mecklenburg-Vorpommern
ምስል picture-alliance/dpa/J. Büttner

በሌላ በኩል ጀርመን ሁለተኛ ዙር የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን እየተጋፈጠች ነዉ ሲል አንድ የጀርመን የሐኪሞች ሕብረት አስጠነቀቀ። ነዋሪዉ ለኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት መገታት የማኅበራዊ ርቀትን እና ጥንቃቄዉን ቸል ባለበት በአሁኑ ወቅት ሃገሪቱ ዉስጥ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ወረርሽኝ ሞገድ እየታየ ነዉ፤ ምናልባትም አደጋዉ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የጠነከረ እና የከፋ ሊሆን ይችላል ሲል ማኅበሩ አሳስቦአል። ባለፈዉ ሳምንት በጀርመን በኮሮና ተኅዋሲ የሚያዘዉ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ከታየ በኋላ ምሁራን የኮሮና ስጭትን ለመግታት ነዋሪዉ አካላዊ ርቀትን እና የእጅን ንጽሕና እንዲጠብቅ እንዲሁም የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛን እንዲያደርግ በድጋሚ ጥሪ ማድረግ መጀመራቸዉ ይታወቃል። በዓለም የኮሮና ተኅዋሲ መረጃ መዘርዝር መሰረት በጀርመን ባለፉት 24 ሰዓታት ዉስጥ ብቻ 509 ሰዎች በኮሮና መያዛቸዉ ተረጋግጦአል። በአሁኑ ወቅት በጀርመን በአጠቃላይ  ከ 211 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል። ኮሮና ባስከተለባቸዉ ሕመም እስካሁን 9226 ሰዎች ደሞ ሞተዋል።  
 


ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ