1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለተኛዉ ዙር የችግኝ ተከላ ዘመቻ

ዓርብ፣ ግንቦት 28 2012

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድር ባለስልጣናትና የሐገር ሽማግሌዎች በጀመሩት በዘንድሮዉ ክረምት ዘመቻ 5 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዷል። ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን የጀመረችዉ ዛሬ በዓለም ቀፍ ደረጃ እየታሰበ ያለዉን የዓለም የአካባቢ ጥበቃ ቀን ምክንያት በማድረግ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3dJt7
Äthiopien Hawassa | Premierminister | Abiy Ahmed
ምስል DW/S. Wegayehu

ሁለተኛዉ ዙር የችግኝ ተከላ ዘመቻ

             
የኢትዮጵያ መንግሥት «የአረንጓዴ አሻራ» ያለዉ ሁለተኛዉ ዙር የችግኝ ተከላ ዘመቻ ዛሬ ሐዋሳ ዉስጥ በይፋ ተጀመሯል።ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድር ባለስልጣናትና የሐገር ሽማግሌዎች በጀመሩት በዘንድሮዉ ክረምት ዘመቻ 5 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዷል።ዘመቻዉ የኮሮና ተሕዋሲን ስርጭት ለመከላከል ከሚወሰደዉ ርምጃና ጥንቃቄ ጋር አይቃረንም ነዉ የተባለዉ።ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ አምና ባነሳሱትና ባስጀመሩት ዘመቻ አምናን ጨምሮ በ4 ዓመታት ዉስጥ 20 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዷል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ዛሬ እንዳሉት አምና ከተተከለዉ ችግኝ 84 በመቶዉ ፀድቋል።

Äthiopien Hawassa | Premierminister | Abiy Ahmed
ምስል DW/S. Wegayehu

 ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ