Recycling በአፍሪቃ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 02.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

Recycling በአፍሪቃ፣

ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፤ ዋና ማዕከሉ በለንደን የሚገኘው «ሮያል ሶሳይቲ» በመባል የታወቀው የተማራማሪዎች ድርጅት ፣ የዓለምንም ሆነ የተፈጥሮን አጠቃላይ ይዞታ ከኤኮኖሚ ጋር በማዛመድ 133 ገጾች ያሉት ዘገባ አቅርቦ ነበር። ባለፉት 2

ዓመታት ፣ የተለያዩ ጠበብት፣ ዓለምን ለብዙኀኑ ኑዋሪዎቿ የተሻለች ለማድረግ፤ ቀጣይነት ወዳለው የኤኮኖሚ ዕድገትም እንዴት መሸጋገር እንደሚቻል የሚያሳዩ ምልክቶችን ያካተቱ የምርምር ጽሑፎችን አቅርበዋል። የምርምር ጽሑፎቹ፤ የቀረቡበትን የ 23 ዓለም አቀፍ የሳይንስ ጠበብት ሰብሰባ፣ በሊቀ-መንበርነት የመሩት ፣ እ ጎ አ በ 2002 ዓ ም ፤ ከሌሎች ሁለት ተመራማሪዎች ጋር የኖቤል ሽልማት ባለቤት የሆኑት እንግሊዛዊው የኅዋሳት ተመራማሪ ፣ Sir John Edward Sulston ናቸው።

ሰልስተን ፣ በዓለም ዙሪያ፣ 1,3 ቢሊዮን የሚሆነውን በቀን ከአንድ ዶላር ከ 25 ሳንቲም ያነሰ ገቢ ያለውን፣ በድህነት የማቀቀ ህዝብ የኑሮ ደረጃ ከፍ ለማድረግ፣ ያቀረቡት ሐሳብ ተቀባይነት ካላገኘ፣ ውጤቱ ከዚህ ቀደም ፍጹም ታይቶ ባልታወቀ ደረጃ እጅግ አስከፊ እንደሚሆን ነውየተነበዩት።

አምና ከ 7 ቢልዮን ማለፉ የተነገረለት የዓለም የህዝብ ቁጥር፣ (ገሚሱ የሚኖረው በከተሞች መሆኑ የታወቀ ነው) እስከዚህ ምዕተ-ዓመት ፍጻሜ ድረስ፤ በአጠቃላይ፤ 10 ቢሊዮን ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በከተሞች የሚኖረው ደግሞ ቁጥሩ ወደ 75 ከመቶ እንደሚንር ነው የሚጠበቀው። የአፍሪቃ የልማት መርኅ ተቋም፣ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ ኤሊያ ሚሲያፋዚ ዙሉ ፣ ወደፊት የዓለም ህዝብ በአማካዩ 70 ከመቶ የህዝብ ብዛት ዕድገት በሚያሳይበት፤ የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ፣ ይበልጥ የተጓደለበት በመሆኑ፣ የቤተሰብ መምሪያ ትምህርት ሊስፋፋ፣ ከላዔ-ጽንስም ፣ በተሻለ መመሪያ ሊቀርብለት ይገባል ባይ ናቸው። ትምህርት፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም ህክምና ይበልጥ እየተስፋፋ ሲሄድ አብነቱ ተፈልጎ አይታጣም።

የሆነው ሆኖ፣ እንደርሳቸው አባባል፤ አፍሪቃውያት ፣ ጥቂት ልጆች ብቻ እንዲኖሯቸው የሚፈልጉ መሆናቸውን የሚያመላክቱ መላ-ምቶች አሉ። ልጅ የመውለድ ዕጣ ፈንታ የሚጎላው፤ ለምሳሌ ያህል ኒዠርን በመሳሰሉ አገሮች ገሚሶቹ ልጃገረዶች የሚዳሩት በ 16 ዓመታቸው በመሆኑ ነው። በለንደኑ ጉባዔ የተገኙት የሳይንስ ጠበብት፤አንዳንድ አስደንጋጭ የሚባሉ መዘርዝር ጥናቶችን ጭምር ነው ያቀረቡት። ለምሳሌ ያህል በኢንዱስትሪ በበለጸጉት አገሮች የሚኖር አንድ ልጅ ፣ በመልማት ላይ ከሚገኙት አገሮች እኩዮቹ ከ 30- 50 እጥፍ ውሃ ይጠቀማል። በዓለም ዙሪያ አማካይ የምግብ «ካሎሪ»፣ እ ጎ አ በ 1969 እና 2005 ዓ ም፤ በ 15 ከመቶ ነበረ ከፍ ያለው።

ይሁንና እ ጎ አ በ 2010 (ከሁለት ዓመት በፊት)አንድ ቢሊዮን ህዝብ ፣ አነስተኛውን ካሎሪ እንኳ የማግኘቱ ዕድልም ሆነ አቅም አልነበረውም። እ ጎ አ እስከ 2007 ፣ በ 47 ዓመታት ውስጥ፣ የተለያዩ ማዕድናት ለምሳሌ ያህል፣ መዳብ፣ እርሳስ፣ ሊትዬምና የመሳሰሉት 4 እጥፍ፣ ለኤሌክትሮኒካ መሣሪያዎች የሚውሉት ታንታለም/ኒዮቢዬም አጠቃቀም 77 እጥፍ ያህል ነው የጨመረው። ሰር ሰልስተን፣ የሳይንስ ጠበብቱ፣ ያቀረቡት ዘገባ መልእክት፣ በተለይ ለበለጸጉት አገሮች ፣ «ጤናማና ደስተኛ ህይወት ለማሳለፍ ብዙ ነገር ማጋበስ አይኖርባችሁም » የሚል ነው ሲሉ ያስረዳሉ። ጥያቄው ፖለቲከኞችና ሸማቹ ህዝብ ምክሩን ይሰማ ይሆን ? የሚለው ነው።

በበለጸጉት አገሮች ከሚመረቱት የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችና መጠን የለሽ የቅንጦት ዕቃዎች ሌላ ማሸጊያው ላስቲክም ሆነ የላስቲክ ቦርሳ በአዳጊ አገሮች እንዲዛመት ተደርጎ፣ ለተፈጥሮ አካባቢ ጠንቅ ስለመሆኑ በየጊዜው ሲነገር እንሰማለን። እየታየም ነው።አፍሪቃ ውስጥ ይኸው አደጋ ከተደቀነባቸው ሃገራት መዲናዎች አንዷ ፤ የጋናዋ አክራ ናት። ግማሽ ሊትር የሚጠጣ ውሃ፣ የተሞላባቸውን ላስቲኮች፣ተጠቃሚው ህዝብ፣ ውሃውን ከጠጣ በኋላ ላስቲኮቹን በየቦታው ስለሚጥላቸው፤ ከተማይቱንና የተፈጥሮ አካባቢን ያቆሽሽ ነበር። እነዚህና ሌሎች ተለቅ ያሉ ፕላስቲኮች፤ፍሳሽ የሚተላለፍባቸውን የከርሠ-ምድር ቧንቧዎች በመዝጋት፤ ፍሳሹ፣ እያፈተለከ ወደ ውጭ በመፍሰስ፣ ከተማይቱን እየበከለ ሲያስቸግር መቆየቱን የተገነዘቡትና መፍትኄ ለመሻት «ትራሽ ባግስ» የተሰኘውን ድርጅት የመሠረቱት የብሪታንያቅ ተወላጅ ስትዋርት ጎልድ፣ እንዲህ ይላሉ።

«ከ 6 ዓመት በፊት ወደ አክራ ስመጣ ፣ በሰፊው የፓላስቲክ ቁሻሻ ክምር፣ በተፈጥሮ ላይ አደጋ ደቅኖ ነበር። ያኔ ፕላስቲኩን መልሶ ለሌላ ጠቀሜታ ማዋያው ዘዴ ገና አይሠራበትም ነበር። በትክክል ቁሻሻ በመሰብሰብ ፣ ይህን ተግባር የሚያከናውንም አልነበረም። እናም አንድ ዘዴ ፈልገን አገኘን ቁሻሻውን ሰብስቦ በፋብሪካ እንደገና ለሌላ አገልግሎት የሚያውል ማለትም የዕቃ መያዣ ቦርሳና የመሳሰለውን ለመሥራት ተነሣሣን።»

ባለፈው መጋቢት በዚህ በቦን ፣ የጀርመን የአካዳሚ የልውውጥ አገልግሎት(DAAD) ባሰናዳው «ለውጥ በተመራማሪዎች ልውውጥ » በሚል ዐቢይ ርእስ ባሰናዳው ጉባዔ ተገኝተው የነበሩት፤

በየቦታው የሚጣል ፕላስቲክ ፤ቆርቆሮም ይሁን የመሳሰለ፤ ለተፈጥሮ ጠንቅ እንዳይሆን ብቻ ሳይሆን ዳግመኛ ለሌላ አገልግሎት እንዲውል ለማድረግ የተደራጁ ክፍሎች ወይም ፋብሪካ ሳይሆን፤ ከህዝብ በኩል በዚህ ረገድ ያለውን ቁጠበና የፈጠራ ችሎታ የሚያደንቁት

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምህንድስና ፤ ህንጻ ግንባታና የከተማ ልማት ተቋም ፕሮፌሰር ፤

ጀርመናዊው ዶ/ር ዲርክ ዶናት፣

«ለምሳሌ ያህል ፣ ስለኃይል ምንጭ የተቀላጠፈ አሠራር፣ ወይም የተጠቀሙበትን ዕቃ መልሶ በፋብሪካ ሠርቶ ፣ ሥራ ላይ ማዋል፤ (Recycling)ኢትዮጵያ ውስጥ ያላንዳች ለውጥ ባለፉት ምዕተ-ዓመታት ሲሠራበት የቆየ ጉዳይ ነው። በጀርመንኛ አባባል፣« የታተመ ፎቶግራፍ እንዲሁአይጣልም» እንደሚባለው መሆኑ ነው፤ ምን አለሽ ተራ፣የገበያ ክፍል ፣ኢትዮጵያ ፣ አዲስ አበባ ውስጥ፣ እዚያ፣ እፁብ ድንቅ የሆነ የ«ሪሳይክሊንግ» ውጤት ያገኛሉ። ልዩ ትልቅ የጥራት መሥካሪ አረንጓዴ ምልክት ፤ ወይም የሆነ ከመንግሥት በኩል የጥራት ምልክት ሳይደረግበት ! ማለት ነው።

በዚያ ማንኛውም የፕላስቲክ መክደኛ ወይም መያዣ፣ ማንኛውም ቆርቆሮ ለሌላ ጥቅም ይውል ዘንድ እንደገና ይሠራል። በአጠቃላይ በእንዲህ ዓይነቱ ጥሬ ነገር (ማቴሪያል)ወይም የሃብት ምንጭ የመጠቀሙ ንቃተ ኅሊና ወጪን የሚጠይቅ፣ ይበልጥ ትርጉም ሰጪ ነውና በዚሁ መጠቀም የሚለው በአርአያነት የሚጠቀስ ነው።

በቤት አሠራር ሥነ-ቴክኒክ ረገድም እንዲሁ! በቀላሉ በማያያዝ ወይም የተፈጥሮ ውጤቶችን፣ ለዘለቄታው እንደሚበጅ አድርጎ መጠቀሙ! ---ምሳሌ መስጠት ይቻላል! ከዚሁ ፤ የቆየ ሥነ-ቴክኒክ ጋር በተያያዘ፣ ወጪ የሚቀንስ ቤት ወይም በዝቅተኛ ዋጋ የሚሠራ ቤትንበተመለከተ ና ስለመሳሰለው ሲነገር ብዙ ነው መማር የሚቻለው። ጭቃና ሣር ሌላ ወይም ሸምበቆ እነዚህን የመሳሰለውን በተፈጥሮ የሚገኙ ጥሬ ሃብቶች፤ ይህ በቦታው የሚገኝ ነው ፤

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 02.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14oIv
 • ቀን 02.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14oIv