Radio D – በራዲዮ ለጀማሪዎች የሚሰጥ የቋንቋ ትምህርት | Radio D | DW | 21.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D

Radio D – በራዲዮ ለጀማሪዎች የሚሰጥ የቋንቋ ትምህርት

በራዲዮ የሚሰጠው የቋንቋ ትምህርት 26 ክፍሎች አሉት። እያንዳንዳቸው 15 ደቂቃዎች ይቆያሉ። የቋንቋ ትምህርቱ ሀሳብ ለቴሌቪዥን ከተዘጋጀው የቋንቋ ትምህርት redaktion D ጋር ተመሳሳይ ነው።

ጀርመንኛ ከ ፓውላና ፊሊፕ ጋር ተማሩ

ጀርመንኛ ከ ፓውላና ፊሊፕ ጋር ተማሩ

ርዕስ፦ በ 26ቱ ምዕራፎች ፓውላና ፊሊፕ ይመሩናል።

ሁለቱ የሬዲዮ የቋንቋ ክፍል- Radio D ጋዜጠኞች በመላው ጀርመን እየዞሩ እንቆቅልሽ የሆኑ ታሪኮችን ይፈታሉ።

ፓውላና ፊሊፕ የኖይሽቫንእሽታይንን ቤተ መንግስት ይጎበኛሉ። እዛም ንጉስ ሉድቪግን ያገኛሉ። ከሀንቡርግ ከተማ ሆነው ስለ አንድ ወደብ ላይ ስለተገኘ አሳ ነባሪ ይዘግባሉ። ከፋሲካ በፊት የሚከበረው በዐል - ካርኒቫል ላይ ደግሞ ሁለቱ ጋዜጠኞች ጠንቋዮች ይተዋወቃሉ …

የሚመለከተው ፦ የ Radio D ትምህርት አንዳችም ችሎታ የሌላቸውን ወይም ደግሞ መጠነኛ የቋንቋ ችሎታ ያላቸውን በተጨማሪም በአውሮፓ ማዕቀፍ የ1ኛ A ደረጃና የ2ኛ A ቋንቋ መማር የሚጀምሩትን ያካትታል።

ቋንቋዎች፦ Radio D በ 16 ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ይቀርባል ( ግማሾቹ ገና በዝግጅት ላይ ናቸው)

በአረቢኛ

በቡልጋሪኛ

በቻይንኛ

በእንግሊዘኛ

በፋርሲ

በፈረንሳይኛ

በኢንዶኔዚኛ

በኪሶዋሊኛ

በክሮአትኛ

በማክሶዲንኛ

በፓለንኛ

በፓርቹጊዢኛ/ የብራዚል

በሮማንኛ

በራሽኛ

በስፓንኛ

በቱርኪኛ

ስለ ስርጭቱ ዝርዝርና የሚሰራጭበትን ቀን ማወቅ ከፈለጉ በአየር ላይ የቀረቡት ቋንቋዎችን ይጎብኙ።