NATO እና የጀርመን የተጓዳኝነት ድርሻ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 02.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

NATO እና የጀርመን የተጓዳኝነት ድርሻ

«ኦይሮፋይተር» የተባለው ዘመናዊ የጦር አይሮፕላን ሰውም ሆነ ዕቃ የሚጫንበት ዋናው አካል እንከን አለበት በማለት ጀርመን ለጊዜው ተጨማሪ ዩውሮፋይተር ከእንግዲህ ላለመግዛት ትናንት ካሳወቀች ወዲህ፤ አይሮፕላኑን በጋራ የሚሠሩት ኩባንያዎች፣ ላጋጠመው

ሳንክ መላ በመፈለግ ላይ መሆናቸውን በዛሬው ዕለት አስታወቁ። አጋጠመ የተባለው ሳንክ፣ ምናልባት የአይሮፕላኑን የአገልግሎት ዘመን ግማሽ -በግማሽ ሊቀንሰው ይችላል ነው የተባለው። አይሮፕ ላኑን በጋራ የሚሠሩት ኩባንያዎች ፣ የብሪታንያው «ኤይሮስፔስ» «ኤርቡስና «አሌንያ ኤርማቺ» ናቸው። «ኦይሮፋይተር » እንከን አለበት ከመባሉ ጋር ተያይዞ፤ ጀርመን ለመከላከያ ተጓዳኝነት ድርሻን በመወጣት ረገድ እስከምን ድረስ አስተማማኝ ናት የሚል ጥያቄም መነሣቱ አልቀረም።

የ«ዩውሮፋይተር» ኩባንያ ዋና አስተዳዳሪ አልቤርቶ ጉቴሬዝ ፣ እንዳሉት ኩባንያው፤ «ታይፉን» የተሰኘውን ዩውሮፋይተር የጦር አይሮፕላን በሚገጣጥምበት ቦታ የጥራት እንከን ስለመከሠቱ ጠንቅቆ ያውቃል ነው ያሉት። ስለ አኤሮፕላኑ እንከን ሲወሳ የተጠቀሰ ዋና ጉዳይ ፣ የአይሮፕላኑ ዋና አካል የብረቱ ወለል በሚገባ እንዲለሰልስ አልተደረገም የሚል ነው።

እ ጎ አ በመጋቢት 1994 በበረራ የተፈተሸውና ከ ነሐሴ 4 ቀን 2003 ዓ ም አንስቶ በይፋ የተዋወቀው ዩውሮ ፋይተር -ታይፉን ፣ መሠራት የጀመረው እ ጎ አ ከ 1983 አንስቶ ነው። ይህን በሰሜን አትላንቲክ ዩውሮፋይተር ና ቶርኔዶ ጦር አይሮፕላኖች አያያዝ ሥር የሚገኝ ፕሮጀክት የሚመሩት 5 አውሮፓውያን መንግሥታት ፣ ብሪታንያ፤ ጀርመን፤ ፈረንሳይ፤ ኢጣልያና ስፓኝ ናቸው። «ዩውሮፋይተር ታይፉን» የጦር አይሮፕላን ገዝተው አየር ኃይላቸውን ያጠናከሩ አገሮች፣ ኦስትሪያ፤ ኢጣልያ፤ ጀርመን፣ ብሪታንያ ፣ እስጳኝ እንዲሁም ስዑዲ ዐረቢያና ኦማን ናቸው። እ ጎ አ ከ 2013 ወዲህ ባጠቃላይ 571 ዩውሮፋይተር ታይፉን ጦር አኤሮፕላኖች ለተለያዩ አገሮች አየር ኃይሎች ተሸጠዋል።

ዩውሮፋይተር ታይፉን ፣ በከፍተኛ ጥረትም ሆነ ደረጃ በቀላሉ የበረራ አቅጣጫውን በመለዋወጥ ከጠላት የጦር አኤሮፕላን ጋር ግብግብ በመግጠም በአሸናፊነት እንዲወጣ የተሠራ ነው።

ከአውሮፓውያኑ የ«ኔቶ» አባላት መካከል በጦር ኃይል ረገድ ከፍተኛ የሆነ አቅምም ፣ ችሎታም ያላት ጀርመን እንደሚጠበቅባት ሆና አልተገኘችም የሚል ትችት እየቀረበባት ነው። በዋሽንግተን ዲ ሲ፣ የ DW ተጠሪ ጌሮ ሽሊስ ያነጋገራቸው ከሪፓብሊካንስ፣ የፔንስልቬንያ የህዝብ እንደራሴ እንዲሁም በ ዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ ፣ ጀርመን የምትገኝበት የሀገራት ቡድን ይዞታ ተመልካች ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ቻርሊ ዴንት ፣ ጀርመን፣ በመከላከያ አቋም ረገድ ብቃት አለማሳየቷን በተመለከተ እንዲሁም በኔቶ የተጓዳኝነት ድርሻ ተዓማኒነትን አጠያያቂ ያደርግባት እንደሁ ተጠይቀው ሲመልሱ--

«ዩናይትድ ስቴትስና ጀርመን ባለፉት ዓመታት እምብዛም ያልተጤነባቸው እንከን ያለባቸው ጉዳዮች ቢያጋጥሟቸውም፣ የተቀራረቡ ወዳጆችና ተጓዳኞች ሆነው ይኖራሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን «እስላማዊ መንግሥት» ያሉትን ታጣቂዎች በመዋጋቱ ረገድ በጀርመን ላይ መተማመን አስቸጋሪ ሆኗል። ዩናይትድ ስቴትስ እዚህ ላይ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ያለው ተጓዳኝ ነው የምትፈልገው። ጀርመን በዚህ ረገድ የተሟላ አቋም ይዛ እንድትቀርብ እንፈልጋለን። መዘንጋት የሌለበት፣ ጀርመን አስተማማኝ የሆነ ብዙ ጦር መሣሪያ እንደምትሸጥ ነው። እዚህም ላይ ነው አጠቃላይ የሆነ ችግር የሚያጋጥመው። በመከላከያ ረገድ ፣ የጀርመን ችሎታ ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራት ሁሉ የላቀ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ለኔቶ የምታዋጣውን ¾ኛ በጀት ጉዳይ እንደገና መመርመር ሳይኖርባት አይቀርም። ካልተጣራ ብሔራዊ ገቢአቸው ሁለት ከመቶ ለመከላከያ የሚያውሉ 3 የአውሮፓ ሃገራት ናቸው። ኢስቶኒያ ፤ ብሪታንያና ግሪክ!»

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍርንክ ቫልተር ሽታይንማየር ባለፈው ቅዳሜ በተባበሩት መንግሥታት አጠቃላይ ጉባዔ አገራቸው በዓለም አቀፍ ፀጥታ ማስከበረ ረገድ ላቅ ያለ ድርሻ እንደምታበረክት ቃል ገብተዋል።ስለ ጀርመን መከላከያ ሠራዊት ትጥቅ ይዞታ ይፋ መግለጫ ወጥቷልና የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩን ተዓማኒነት አጠራጣሪ የሚያደርግ ሁኔታ ተፈጥሮ ይሆን?

Symbolbild Nato

« አይ! አይመስለኝም። ው ጉ ሚ ሽታይንማየር የሚያምኑበትን ነው የተናገሩት። ይሁንና ጀርመን የፀጥታ አጠባበቅን በተመለከተ ከፍ ያለ ድርሻ ማበርከት ትሻለች። ማለታቸው በአሁኑ ሰዓት በጎ ፈቃደኝነትን ከመግለጽ ያለፈ አለመሆኑን ነው መገንዘብ የሚቻለው።»

የጀርመን መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ሹም ሐራልድ ኩያት ፣ ይህ ጀርመን ለመሰለ ትልቅና በኤኮኖሚም ለደረጀ ሀገር አሳፋሪ ነው ብለዋልና በዚህ አነጋገር ይስማማሉ?

«ጀርመን የመከላከያ ችሎታዋን ይበልጥ ከፍ ማድረግ የክብርና ለራስ ዋጋ የመስጠት ጉዳይ ነው። የአሜሪካ ሕዝብ እስከመቸ ድረስ የዩናይትድ ስቴትስን በተናጠል ከባድ qm,ንበር የመሸከም ጣጣ እንደሚቀበለው አላውቅም። ጀርመን እጅጉን በአነስተኛ ደረጃ ነው አቅሟን የምታሳየው። አገሪቱ ላቅ ያለ ችሎታና አቅም አላት ማሳየት ያለባትም በዚያው መጠን ነው። አንድ ጎረምሳ ፣ ቀላል ክብደት ብቻ ማንሳቱን ከቀጠለ ጥሩ አይሆንም።»

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic