1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

M 23 ከያዛቸው አካባቢዎች መልቀቅ መጀመሩ

ረቡዕ፣ ኅዳር 19 2005

ባሳለፍነው ሳምንት በምስራቅ ኮንጎ የምትገኘውን የጎማ ከተማና ባከባቢዋ የሚገኙ መንደሮችን የተቆጣጠሩ አማጺያን ከያዙት አከባቢ ለቀው እየወጡ መሆናቸውን ምልክቶች መታየት ከምረዋል። የአማጺያኑ ከጎማ መውጣት ዜና የተሰማው ከትናንት ወዲያ በአማጺያኑ

https://p.dw.com/p/16sBL
ምስል Reuters

የጦር መሪና በምስራቅ አፍሪካ ቡድን የጦር አዛዦች መካከል በዩጋንዳ መዲና በካምፓላ በተደረገው ስምምነት ነበር። በነገው እለት አማጺያኑ ጎማን ሙሉ በሙሉ እንደሚለቁ ይጠበቃል። ዝርዝሩን ገመቹ ያቀርብልናል።

የM23 አማጺያን አመጽ፣ በብዚ ሺ የሚቆጠሩ የምስራቅ ኮንጎ ዜጎች ከቀዬያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል። በቅርቡ አማጺያኑ ዲሞክራሲያዊ ኮንጎን ለመቆጣጠር ያደረጉት ፈጣን የጦር ዘመቻ ምናልባት አሁንም ሌላ ግጭት ይቀሰቅሳል የሚል ስጋት ፈጥሮ ነበር።

Kongo - Rebellenführer Jean-Marie Runiga
ምስል Reuters



የM23 የጦር መሪን ሱልጣኒ ማኬንጋን ጠቅሶ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ባሳለፍነው ሰኞ በካምፓላ ዩጋንዳ በተደረሰው ስምምነት መሰረት፣ አማጺያኑ ቢበዛ በሶስት ቀናት ውስጥ ከጎማ በ20 ኪሎመትር ርቀው መውጣት ይኖርባቸዋል። የዩጋንዳ ጦር አዛዥ አሮንዳ ንካይሪማ፣ አማጺያኑ የፊታችን ሐሙስ ረፋድ ላይ ጎማን ሙሉ ለሙሉ ለቀው እንደሚወጡ በትናንትናው እለት ተናግረዋል፣

«የመከላከያ ኃይሉ ኃላፊ፣ ከኮንጎ ጦር ኃልይና ከM23 አማጺያን አመራሮች ጋር ትናንት ተገናኝተው፣ M23 ጎማን ለቆ የመውጣት እቅድ እንደሚጀምር አሳውቀዋቸዋል። ይህን ነበር ትናንት የተወያየነው። ዛሬ እኩለ ቀን ላይ፣ የM23 አማጺያን ከጎማ ወጥተው አንዳንድ ወታደራዊ ጠቀሜታ ወዳላቸው ይዞታዎች መሄድ ይጀምራሉ። የአውሮፕላን ማረፊያውን የተቆጣጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች እዚያው ይቆያሉ። ከተማዋን የመልቀቁም ሂደት በ48 ሰዓታት ውስጥ ይጠናቀቃል።»

ጎማን የመልቀቁ ስምምነት በዩጋንዳ ዋና ከተማ ከተደረሰ ወዲህ፣ የምስራቅ አፍሪቃ የጦር አዛዦች፣ የኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ለመልቀቅ ስለተደረሰው ስምምነት አፈጻጸም ለመመርመር የፊታችን ዓርብ ጎማ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አማጺያኑ ከጎማ በስተሰሜን ወደምትገኘውና ዩጋንዳንና ሩዋንዳን በሚያዋስነው አከባቢ ወዳለችው የM23 ጠንካራ ይዞታ ወደ ሆነችው የሩትሹሩ ግዛት የጦር ትጥቅና የመድሃኒት አቅርቦቶቻቸውን ማጓጓዝ ጀምረዋል።


በኒውዮርክ የሚገኙት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ኃይል አዛዥ ሄርቬ ላድዞ አማጺያኑ ከከተማው መውጣት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል።

የM23 አማጺያን ከጎማ እንዲወጡ ከመወሰኑ በስተቀር የተኩስ አቁም ስምምነት እስካሁን አልተደረሰም። በሌላ በኩል የM23 አማጺያን የፖሊቲካ ኃላፊ ዦን ማሪ ሩጋ ፣ የኮንጎ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ አማጺያኑ የጠየቁትን ሲያሟሉ ብቻ ከጎማ እንደሚወጡ ተናግረዋል፣

«ሚስተር ካቢላ በህዳር ወር ከተካሄደው ምርጫ በኋላ እስር ላይ ያሉትን ኤትዬን ቺሴኬዲን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሁኑኑ ከእስር ይፍቱ እላለሁ። በሁለተኛ ደረጃ ሁሉም የፖሊቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንፈልጋለን። በቼበዬ ግድያ ጉዳይ የሚጠረጠሩ ጆን ሙምቢም እንዲታሰሩ እንፈልጋለን።

ጆን ሙምቢም የካቢላ ታማኝ ናቸው የሚባሉ የፖሊስ እንደራሴ ሲሆኑ፣ ቼባዬ ከተባሌው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግድያ ጋር በተያያዘ ይጠረጠራሉ። ኢትዬን ቺሴኬጂም ከወራት በፊት በኮንጎ በተደረገው ምርጫ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲን ወክለው ተወዳድረዋል። ነጻ መሆኑ በሚያጠራጥር ምርጫ ተቃናቃኛቸው ካቢላ አሸንፈዋል ቢባልም፣ ቺሴኬጂ ግን ራሳቸውን በራሳቸው አሸናፊ ነኝ ብለው አውጀው ነበር።

በኮንጎ ለተካሄዱ ግጭቶች ፍጻሜ ለማስገኘት እአአ በ2009 የተደረሱ ስምምነቶች ተፈጻሚ አልሆኑም በሚል ተቃውሞ ነበር የM23 አማጺ ቡድን ባሳለፍነው የፈረንጆች ሚያዚያ ወር ከዲሚክራያዊ ኮንጎ ጦር ተገንጥሎ የወጣው። በኮንጎ ውስጥ በየጊዜው የተቀሰቀሱ ግጭቶች ብዙ ሰዎችን ለህልፈተ ህይወት ቢዳርጉም፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እስካሁን በርግጥ ምን ያህል እንደሆኑ አይታወቅም።
ገመቹ በቀለ
አርያም ተክሌ

M23 Rebellen Goma Kongo Afrika
ምስል dapd
M23 Rebellen in Goma Kongo
ምስል picture-alliance/dpa
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ