«IS» እና የኧልቃይዳ ግንኙነት | ዓለም | DW | 07.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

«IS» እና የኧልቃይዳ ግንኙነት

በኢራቅና በሶርያ ከባድ ጫና እያረፈበት የሚገኘዉ ራሱን «እስላማዊ መንግሥት» ሲል የሚጠራዉ ጽንፈኛ ቡድን ሰሜናዊትዋ ኢራቅ ከተማ ሞሱል እንደሆነዉ፤ ሁሉ ከቀን ወደቀን የተቆጣጠረዉን ቦታ በመልቀቅ እየሸሸ ይገኛል።  ቀደም ሲል አሸባሪ ቡድኖች ጥቃት በመጣል አካባቢዉን ይቆጣጠሩና ያስተዳድሩ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:05

የ«እስላማዊዉ መንግሥት» እና የ«ኧል-ቃይዳ» ግንኙነት

 

ከዩናይትስ ስቴትስ አሜሪካና ኢራቅ በተደጋጋሚ እንደሚሰማዉ ይፋዊ መግለጫ የኢራቅዋ ሞሶል ከተማ እራሱን  «እስላማዊ መንግሥት» ብሎ ከሚጠራዉ አሸባሪ ቡድን እና በአጠቃላይ ከእስላማዊ አክራሪ ጽንፈኞች በቅርቡ ትፀዳለች። የዶይቼ ቬለዉ ቦይሮን ብላሼክ እንደዘገበዉ ደግሞ ጽንፈኛ ቡድኖች «እራሱን እስላማዊ ቡድን» ከሚለዉ አሸባሪ ቡድን ጋር ዉኅደት ሳይፈጥሩ አልቀረም ። ከቅርብ ቀናት በፊት  የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ጀምስ ማቲስ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተናገሩትን እንዲህ ሲሉ ገልፀዉ ነበር።    

« አንድ ስልታዊ የሆነ የዘመቻ ለዉጥ አዘዋል። ራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራዉ ቡድን የተቆጣጠራቸዉን ቦታዎች ለማስለቀቅ ትግል ከማድረግ፤ ጠላቶችን እዝያዉ ባሉበት ቦታማዉደም ነዉ ። እንዲህ ነዉ « IS»ን ማጥፋት የሚቻለዉ» 

ይህ ስልት ግን አጠራጣሪ ነዉ። በዚህ ዓይነቱ ስልት በሞሱል ከተማ

የሚገኙት የ«IS» ተዋጊዎች በሙሉ ሊገደሉና መቃብራቸዉ ሊገኝ ይችላል። የተዋጊዎቹ ብቻም ሳይሆን የመሪያቸዉ የአቡ በከር ኧል ባግዳዲ ሪሳም ሊገኝ ይችላል። ግን ኧል- ባግዳዲ ሞሱል ከተማ  ግዛታችን ነዉ ሲል ማወጁ ይታወቃል።

ስለዚህም የሞሱል ከአሸባሪዉ ቡድን ነጻ መሆን በኢራቅ አሸባሪዉ ቡድን «IS» ተንኮታኩቶ ወደቀ አበቃለት ማለት አይደለም። እራሱን «እስላማዊ መንግስት » ብሎ የሚጠራዉ አሸባሪ ቡድን ሞሱል ከተማ ሽንፈት ገጥሞት ከተማዋ ከአሸባሪ ቡድኑ ነፃ ብትወጣም፤ የቡድኑ በርካታ ተዋጊዎች በሌሎች የኢራቅ አዉራጃና ግዛቶች በተለይ ደግሞ በምድረ በዳማዉ የኢራቅ ሰሜናዊ ክፍል መሽገዋል።   

በሌላ በኩል በኢራቅዋ ጎረቤት ሶርያ የ«IS» መናገሻ ነዉ በሚባልበት በራካ ከተማም «IS» ይዞታዉን  እያጣ ነዉ። ዬናይትድ ስቴትስ አሸባሪ ቡድኑን ከራካ ከተማ ለማስወጣት በሚደረገዉ ትግል ዋንኛ ተካፋይ ስትሆን ከዚህ ትይዩ በዚሁ ትግል የኩርድ ሚሊሽያዎችን ታስታጥቃለች። ይህንኑ በተመለከተ የዋይት ሃዉስ ቃል- አቀባይ ሴን ስፓይሰር ይህን ተናግረዋል።

«እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራዉን አሸባሪ ቡድን በነጻ ለማሸነፍ፤ የሶርያ ኮርዶች አማጽያን ኅብረት እጅግ አስፈላጊ ነዉ። 

የሶርያ እና የኢራቅ ድንበር «እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራዉ ብድን ታድሶ በአዲስ እራሱን የሚቋቁምበት  ቦታ ሊሆን ይችላል።  ኢራቅ ኧል-ቃይዳ የተመሰረተበት ቦታ ሲሆን ከኧል-ቃይዳ «እራሱን እስላማዊ መንግሥት»  ሲል የሚጠራዉ ጽንፈኛ ቡድን መወለዱ ይታወቃል።

አንድ የነበሩት ሁለቱ ቡድኖች በጎርጎረሳዊ 2013 ዓ.ም ተከፈሉ። በኧል-ባግዳዲ እና በኦሳማ ቢንላደን ተከታይ በአይማን ኧል- ዛዋህሪ መካከል የነበረዉ አንድነትም ፈረሰ።  ከዝያን ጊዜ ጀምሮ በሶርያ እና ኢራቅ በሚገኘዉ የ«IS» ቡድን ላይ ጫና እየበረከተ ከመጣ በኋላ ለሁለት የተከፈሉት ጽንፈኛ  ቡድኖች መቀራረብ እያሳዩ እንደሆነ ተሰምቶአል። የኢራቁ ምክትል ፕሬዚዳንት ላያድ ኧላአዊም ይህኑ ነዉ ያረጋገጡት። 

በ«IS» እና በኧል-ቃይዳ መካከል ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ርግጠኛ ከሆነ ምንጭ ደርሶናል።»  

በኢንተርኔት የተለቀቀ አንድ የቪዲዮ መረጃ እንደሚያሳየዉ ከሆነ የኧል-ቃይዳዉ አይማን ኧል-ዛዋሪ በሶርያ ለሚገኙ ተከታዮቹ የመቀራረብ ሙከራ ሲያደርጉ  የሚታይበት መልክት አስተላልፎአል።

« ከወንድሞቻችሁ በሶርያ ከሚገኙ ጀሃዲስቶች እንዲሁም በመላ ዓለም ከሚገኙት ሁሉ አንድ መሆን ይኖርባችኋል።  በዓለም ዙርያ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ የመስቀል ጦርነት መከፈቱን እያየን ነዉ።»

የኧል-ቃይዳዉ  መሪ ኧል-ዛዋሪ እና የ «IS» መሪ ኧል- ባግዳዲ አንዱ ለአንዱ የጥምረቱን  ዋና የመሪነት ቦታን መልቀቅ ስለማይፈልግ  እስካሁን ዉኅደቱን እዉን መሆን ግን አልቻለም። ከሁለት አንዱ  በጦርነት ቢገደል አልያም በሌላ ምክንያት ቢሞት  ግን ይህ እክል ሆኖ በመሃል የቆመ ጉዳይ መፍትሄ የሚያገኝና ሁኔታዉ የሚቀየር ይመስላል።    

ጽንፈኛ ቡድኑ «IS» እና ኧል-ቃይዳ ከቀድሞ ይልቅ በአሁኑ ጊዜ በሚያራምዱት ሃሳብ መቀራረብን እያሳዩ ነዉ። ቀደም ሲል የኧል-ቃይዳ  ኢላማ የሩቅ ጠላት የሚለዉን ማጥቃት ነበር።  ለምሳሌ ዬናይትድ ስቴትስ አሜሪካን።  «IS» ደግሞ የቅርብ ጠላቶች የሚላቸዉን መንግሥታት፤  አካባቢና፤ ጀሃዳዊዉን ቡድን መቀላቀል የማይፈልጉ ሰዎችን ማጥቃት ነበር። 

«እስላማዊ መንግሥት » እያለ ራሱን የሚጠራዉ አሸባሪ ቡድን ወደ አዉሮጳ ሰርጎ ገብቶአል፤ ለዚህ በምሳሌነት በብሪታንያ የማንችስተር እና የለንደኑ ጥቃት  የቅርብ ጊዜ  ተጠቃሽ ነዉ። አሸባሪዉ «እስላማዊ መንግሥት » በዓለም ዙርያ  የቡድኑን ሃሳብ  ከማያራምዱ ሁሉ ጋር ጦርነትን አዉጆአል።

 

ሞሱል ከ «IS» ቡድን መለቀቅዋን ተከትሎ የቡድኑና የኧል-ቃይዳ ዳግም ጥምረት ብሎም የሌሎች አሸባሪ ቡድኖች ዳግም ዉኽደት ሊከሰት ይችላል። በተለይ ደግሞ የአማጽያኑን አስተሳሰብ እና የፖለቲካ ርምጃ መቀየር ካልተቻለ የበለጠ ችግር ሊገጥም ይችላል።  የኢራቁ ምክትል ፕሬዚዳንት ልያድ ኧላዊም በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ።

 

« በዚህም ምክንያት ነዉ ፤ አማጽያኑን ከመዋጋታችን በተጨማሪ አንድ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን ማካሄድ ይኖርብናል። ይህን ካላደረግን ግን ከ«IS እና ከኧል-ቃይዳ የበለጠ አደገኛ ችግር ይገጥመናል።»

ቦይሮን ብላሼክ  /  አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

 

Audios and videos on the topic