HRW እና የደቡባዊው ኦማ ሸለቆ ነባር ተወላጆች፣ | ኢትዮጵያ | DW | 20.06.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

HRW እና የደቡባዊው ኦማ ሸለቆ ነባር ተወላጆች፣

በደቡባዊው የኦሞ ሸለቆ፤ ለሸንኮራ ተክል ሲባል ቦታ እንዲለቁ ያስገደዳቸውን በሺ የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮችን ከርስት ጉልታቸው እያፈናቀለ ነው ሲል ፣ ከሰሞኑ ባቀረበው ዘገባ ላይ መክሰሱ የሚታወስ ነው። በደቡባዊው ኦሞ ሸለቆ

በደቡባዊው የኦሞ ሸለቆ፤ ለሸንኮራ ተክል ሲባል ቦታ እንዲለቁ ያስገደዳቸውን በሺ የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮችን ከርስት ጉልታቸው እያፈናቀለ ነው ሲል ፣ ከሰሞኑ ባቀረበው ዘገባ ላይ መክሰሱ የሚታወስ ነው። በደቡባዊው ኦሞ ሸለቆ ለዘመናዊ እርሻ ተብሎ 100,000 ሄክታር ያህ ል መሬት፤ ለሸንኮራ አገዳና ለጥጥ ተክል መመደቡ የተነገረ ሲሆን፣ HRW እንዳለው ፣ ቁጥራቸው በ 5 ሺ እና 10,000 የሚገመት አርብቶ አደሮች ተፈናቅለዋል። በዚያ የሚኖሩት በግብርናና በአርብቶ አደርነት የተሠማሩት ሰዎች ህይወት እንዲሻሻል ፣ ህልውናቸው ፣ንብረትና ባህላቸው እንዲጠበቅ ፤ HRW ምንድን ነው ይበጃል የሚለው?
ተክሌ የኋላ በለንደን የ HRW የምሥራቅ አፍሪቃና የአፍሪቃው ቀንድ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ተመራማሪ የሆኑትን ቤን ሮውሌንስን አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሯል።

በኦሞ ሸለቆ ከሚኖሩት 200,000 ያህል ሰዎች አብዛኞቹ ፣ በግብርናና በአርብቶ አደርነት የሚተዳደሩ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ጊቤ 3 የሚሰኘውን የግድብ ሥራ የሚገፋበት መሆኑና በታኅታይ ኦሞም ለሸንኮራና ለጥጥ ተክል መሬት ዓለማለሁ ብሎ መነሣሣቱ ፤ SERVIVAL INTERNATIONAL የተሰኘውን ድርጅትና ሌሎችንም የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች አሳስቧል። እናንተና መሰል ድርጅቶች፤ በአርብቶ አደሮቹ ኅልውና ላይ ሥጋት መደቀኑን ስትገልጡ ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ፕሮጀክቱ የሰዎቹን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ይበጃል ነው የሚለው። የትኛው ነው አሳማኝ መግለጫ? የ HRW የምሥራቅ አፍሪቃና የአፍሪቃው ቀንድ ከፍተኛ ተማራማሪ ቤን ሮውሌንስ-

http://www.hrw.org/logo/images/01_l.gif

-
«ሁለቱም ጉዳዮች ትክክል ናቸው። ግድቡ፤ ኤሌክትሪክ ያመነጫል፤ በመስኖ የሚለማው ሰፊ እርሻም ስኳር ይመረትበታል። ለሠራተኞች የሥራ ዕድል ይሰጣል። ለኢትዮጵያ መንግሥትም የውጭ ምንዛሩሪ ያስገኝለታል።
እኛ ችግር አለ የምንለው፤ ከአሠራሩ ሂደት ላይ ነው። አገሮች ሁሉ ወደ ውጭ ለገበያ የሚያቀርቡትን ማስፋፋት ይሻሉ። ማልማት ይፈልጋሉ ነገር ግን ሁሉም አገሮች፣ ህግ አላቸው ግዴታም እንዲሁ! ልማቱ፣ ለውጡ፤ ህጋዊ መሆኑን በዚያ አካባቢ የሚኖሩትን ሰዎች እንዲጠቅም የተባለው ፕሮጀክት፣ መብታቸውን የሚያስከብር መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።
በኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት አርብቶ አደሮች፣ ከመሬታቸው በግዴታ ያለመልቀቅ መብት አላቸው። በዓለም አቀፍ ህግም አገሮች በመላ፣ መንግሥታት ፤ ህዝብን ማማከር ይጠበቅባቸዋል። ወደ ሌላ ቦታ የሚያዛውሯቸው ከሆነም፤ በሰዎቹ ፈቃደኛነት ነው መፈጸም ያለበት። ለተወሰደ መሬትም ካሣው ሊከፈላቸው ወይም በልዋጭ ሌላ ሊሰጣቸው ይገባል። ይህ ነው እንግዲህ እኛን ያናገረን። ምርጫ የተሰጠ አይመስለኝም። ሂደቱ በትክክል መከናወን ይኖርበታል።»
በደቡባዊው ኦሞ ነባሮቹ የአካባቢው ተወላጆች፤ ለግብርና ልማት ሲባል ስለመፈናቀላቸው የታሠሩና የተደበደቡም ስለመኖራቸው በዜና አውታሮች ይነገራልና ፤ HRW ይህን ማረጋገጥ የሚችልበት ዕድል አለው?

-
«ከኢትዮጵያ ጥርት ያለ መረጃ ማግኘት ከባድ ነው። ምክንያቱም መንግሥት ጨቋኝ ፤በመገናኛ ብዙኀን ላይ የመንግሥት ባልሆኑ ድርጅቶች (NGOs)በተለይ በውጭዎቹ NGOs ላይ ጠጣር እርምጃ የሚወስድ መሆኑ የታወቀ ነው። ከ 2 ዓመት በፊት፣ በደቡባዊው ኢትዮጵያ 40 የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶችን ነው መንግሥት እንዲዘጉ ያደረገው። አዲስ የ NGO ህግም አስተዋውቀዋል። ከዚህ ሌላ ጥቂት የሳቴላይት መረጃዎችን አግኝተናል።ስዕሎቹ በግልጽ የሸንኮራ አገዳ ተክል በአካባቢው ነባር ህዝብ መሬት ላይ መተከሉን በግልጽ ያሳያል። የመስኖ መሥመሮችም ወደሚፈለገው ቦታ መዘርጋታቸውን ያሳያሉ። ከአየር, የተነሱት ፎቶግራፎች፤ በዚያ ምን እየተደረገ እንደሆነ የምንሰማውን ያረጋገጡ ናቸው።»
የኢትዮጵያ መንግሥት የነባሩን ህዝብ ኅልውና የሚያናጋ ተግባር እንዳይፈጽም ማነው ሊያግባባው የሚችል?ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ካላቸው ምዕራባውያን ሀገራት መካከል አንዱ የብሪታንያ መንግሥት ነው። የብሪታንያ መንግሥት በዚህ ረገድ ምንድን ነው ማድረግ የሚችለው ይላሉ?
«የብሪታንያ መንግሥት ብቻ አይደለም። ለኢትዮጵያ መንግሥት፣ ዋንኞቹ ለጋሽ አገሮች ብሪታንያ፣ ሁለተኛ ጀርመን ፤ ከዚያም ኔደርላንድ፤ እንዲሁም የአውሮፓው ኅብረት ናቸው ዋና ዋናዎቹ! ዩናይትድ እስቴትስና የዓለምን ባንክ ጨምሮ ማለት ነው። ስለዚህ ዋንኞቹ ለጋሾች በአርግጥ ልዩ ኀላፊነት አለባቸው። ምክንያቱም ለኢትዮጵያ እርዳታ ሲሰጡ፣ ገንዘቡ በአገሪቱ ማዕዘናት ለሚገኙ ለአውራጃዎች መስተዳደር ሲሆን የሚውለው። የመስተዳደሮቹ ኀላፊዎችም ናቸው በቀጥታ የሠፈራውን መርኀ ግብር የሚቆጣጠሩ! መገልገያ ጣቢያዎችን የሚያዘጋጁ፣ ያለሰዎቹ ፈቃድ አዳዲስ የሠፈራ መንደሮችን የሚቆረቁሩም እነርሱው ናቸው። ስለዚህ የጀርመን መንግሥት፤ የብሪታንያ መንግሥትና ሌሎቹ

-

መንግሥታት በእነዚህ አዳዲስ የመጠለያ ሠፈሮች ግልጋሎት እንዲሰጥ ገንዘቡን እነርሱው ናቸው እነርሱ ናቸው የሚከፍሉት ። ታዲያ በእጅ አዙርም ቢሆን ለነዚህ ሰዎች መፈናቀል ሃላፊነት አለባቸው እናም መንግሥታቱ የኢትዮጵያን መንግሥት ላቅ ያለ ሃላፊት እንዲሰማው ሰብዓዊ መብትን በይበልጥ እንዲያከብር ጮክ ብለውና በግልፅ ማሳሳበብ ይጠበቅባቸዋል ። በእርዳታ አሰጣጥም ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል ። ገንዘባቸው ከመፈናቀል በኋላ በሚከናወን የሠፈራ መርሃ ግብር ማስፈፀሚያ እንዳይሆን በአንድ በኩል እንዳልከው ፣ የኢትዮጵያን መንግሥት ማሳመን ይችላሉ ። ፕሮጀክቱን እርግፍ አድርጎ እንዲተው ሳይሆን በትክክል ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ህግን ተከትሎ እንዲሰራበት ለማድረግ ነው ። »

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 20.06.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15IiM

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 20.06.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15IiM