88ኛዉ ኦስካር በኢትዮጵያዊው ዕይታ | ባህል | DW | 03.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

88ኛዉ ኦስካር በኢትዮጵያዊው ዕይታ

በዩኤስ አሜሪካ የስዕል ጥበብና ሳይንስ ማዕከል የሚዘጋጀዉ ዓመታዊ የፊልም ዘርፍ ሽልማት ማለት የ«ኦስካር» አሰጣጥ ሥነ- ስርዓት ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ለ88ኛ ጊዜ ተካሂዶአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 16:40

ግዙፉ የዓለም የፊልም ዘርፍ ሽልማትና የኢትዮጵያ ፊልም

ምርጥ ፊልም፤ ምርጥ የፊልም ዳይሬክተር ፤ ምርጥ የፊልም መሪ ፤ ምርጥ ዘጋቢ ፊልም ለመሳሰሉት የፊልም ሥራ ዘርፎች ሽልማት የተሰጠበት በሎስ አንጀለስ ላይ የተካሄደዉ የዘንድሮዉ የኦስካር መድረክ ሽልማቱ ነጮችን ብቻ ያሰበሰበ ነው

መባሉ፤ ከሽልማቱ ባሻገር ትኩረትን የሳበ የመነጋገርያ ርዕስ ነበር። ይህንኑ ትችት ሽልማቱ መድረክ መሪ እዝያዉ መድረኩ አስተጋብቶታል። በለቱ ዝግጅታችን የሰሜን አሜሪካዉን የስዕል ጥበብና ሳይንስ ማዕከል የ88ኛ የሲኒማ ጥበብ ሽልማት ሥነ-ሥርዓትን እየቃኘን ከአንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ የፊልም ሥራ ባለሞያ ጋር የኢትዮጵያዉያን የፊልም ሥራ እድገት እንቃኛለን።

ባለፈዉ እሁድ ዩኤስ አሜሪካ ሎሳንጀለስ ላይ ለ88 ተኛ ጊዜ በተካሄደዉ የኦስካር ሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት ላይ «ስፖት ላይት» የተሰኘዉ ፊልም የዘንድሮዉ ምርጥ ፊልም በመባል ተሸልሞአል። በፊልም ሥራ አዋቂዉ በቶም ማክካርቲ የተሰራዉ የዚህ ፊልም ታሪክ በጋዜጠኞች የመረጃ ምርመራ በሰሜን አሜሪካ በአንድ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ዉስጥ በሕፃናት ላይ የተፈፀመ የጾታ ጥቃት ዉዝግብን ይተርካል። ከዚህ ቀደም የኦስካር ሽልማትን ያገኙት የሜክሲኮዉ ተወላጅ አልህሳንድሮ ጎንዛለዝ «The Revenant» በተሰኘዉ የብቀላ ተዉኔት ፊልም ምርጥ የፊልም ዳይሪክተር በመባል ለሁለተኛ ጊዜ ኦስካር ሽልማትን አግኝተዋል። በፊልም መሪ ተዋናይነት ታዋቂዉ የፊልም አክተር ሊዮርናዶ ዴካብርዮ ከስድስት ጊዜ የሽልማት እጩ ነት በኋላ ሆኖ የኦስካርን ሽልማትን የመቀበሉ ዜና የሚዲያዉን ቀልብ ስቦ ነዉ ያመሸዉ።

ታይታኒክ በተሰኘ ፊልም ላይ እጅግ እዉቅናን ያገኘዉ ሌዮርናዶ ዴካብርዮ ሽልማቱን ለመቀበል መድረክ ላይ ወጥቶ የምስጋና መልክቱን ሲያስተላለፍ፤ በዓለም ላይ የሚታየዉን የሙቀት መጠን ለመቀነስ ጥረት እንዲደረግ ሲል ነበር መድረኩን በመጠቀም ጥሪን ያስተላለፈዉ።

« The Revenant የተሰኘዉ ፊልም የሰዉ ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለዉን ግንኙነት የሚያሳይ ነዉ። በጎርጎረሳዊዉ 2015 ዓ,ም በዓለማችን እጅግ ሞቃማታማ ጊዜ የተመዘገበበት ነዉ። ለፊልሙ ቀረፃ በረዶዋማ አካባቢን ለማግኘት ወደ ደቡባዊዉ የዓለማችን ክፍል መሄድም ነበረብን ። የከባቢ የአየር ሁኔታ መቀያየር እዉን መሆኑ በአሁን ጊዜ የምናየዉ ክስተት ነዉ።»

የጀርመን ዘር ሃረግ እንዳለዉ የተዘገበለት ታዋቂዉ አሜሪካዊ የፊልም አክተር ሌዮርናዶ ዴካብርዮ ከሽልማቱ በኋላ በተደረገዉ ድግስ ላይ ኦስካር ሽልማቱን እተቀመጠበት ወንበር ላይ ረስቶት መሄዱ ሌላዉ ሚዲያዉ በስፋት የዘገበበት ፈገግ የሚያሰኝ ጉዳይም ነበር። ታድያ ምን ያድርግ ይህን ሽልማት ከስድስት ጊዜ እጩነት በኋላ በማግኘቱ ነዉ እያሉም ሚዲያዎች በተለያየ መንገድ ዘግበዉለታል። በታይታኒክ ፊልም ኬትን ሆና አክተር ፤ ዴካብርዮ በማሸነፉ የደስታ እንባን በማንባት ደስታዋን ገልፃለች።

ለ88 ተኛ ጊዜ በዩኤስ አሜሪካ የስዕል ጥበብና ሳይንስ ማዕከል በተዘጋጀዉ ዓመታዊ የፊልም ሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት ላይ ምርጥ ፊልም በመባል የተሸለመዉ የዩኤስ አሜሪካዉ « Spotlight » የተሰኘዉ ፊልም በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር 2015 ዓ,ም በቬኒስ ፊልም ፊስቲቫል ላይ ነበር ለመጀመርያ ጊዜ ለተመልካች የቀረበዉ። በእዉነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ እንደተሰራ የተዘገበለት ይህ ፊልም ጋዜጠኞች በአንድ የካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ዉስጥ በሕጻናት ላይ የሚፈፀምን የወሲብ ጥቃትን ሲያጋልጥ ያሳያል። ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ በጀርመን የፊልም ቤቶች መታየት የጀመረዉ ይህ ፊልም በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ማግኘቱም ተዘግቦለታል።

በሽልማት አሰጣጡ ሥነ-ሰርዓት የስዊድንዋ አሊሻ ቪካንደር «ዘ ዳኒሽ ገርል» በተሰኘዉ ፊልም ምርጥ ረዳት ሴት አክተር ሆና የኦስካር ሽልማትን ተቀብላለች። በጎርጎሳዉያኑ 2011 ዓ,ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችዉ እንጊሊዛዊትዋ ሙዚቀኛ ኤሚ ዋይንኃውስ የሕይወት ታሪክን የሚያሳየዉ «ኤሚ» የተሰኘዉ ዘጋቢ ፊልም ምርጥ ዘጋቢ ፊልም በመሆን ተሸልሞአል። «ሰን ኦፍ ሳኦል» የተሰኘው አዉሽቪትስ በተሰኘዉ የናዚ ማጎርያ ቦታ አንድ አይሁድ ላይ የደረሰ ስቃይን የሚተርከዉ የሃንጋሪ ፊልም ምርጥ የዉጭ ሃገር ፊልም በተሰኘዉ ዘርፍ የዘንድሮዉን የኦስካር ሽልማትን ተቀብሎአል።

የወሰቢ ጥቃትን በተመለከተ በዚሁ የሽልማት መድረክ ላይ ሙዚቃን ያቀነቀነችዉ ታዋቂዋ አሜሪካዊት ሙዚቀኛ ሌዲ ጋጋ በአዳራሹ ተሰብስቦ የነበረዉን ታዳሚ በሙዚቃዋ ኮርኩራለች ከፍተኛ ጭብጨባም ተቸራለች። የ88ኛው የኦስካር ሽልማት እጩዎች ስም ዝርዝር ይፋ ከሆነ በኋላ ምንም አይነት ጥቁር ተሸላሚ ባለመቅረቡ ግዙፉ የሽልማት መድረክ ገና ከመጀመርያዉ ከፍተኛ የትችትና ቅሪታ ጥላ አጥልቶበት ነዉ የጀመረዉ። ታዋቂዉን የሆሊዉድ አክተር ጆርጅ ክሎኒን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ የፊልም ተዋናዮች ተቃዉሞ ማድረጋቸዉም ተዘግቦአል። የሽልማቱ መድረክ « የነጮች » ነዉ የሚለዉ ትችት የሽልማት መድረኩ መሪ የነበረዉ ታዋቂዉ ኮማኪና ተዋናይ ክሪስ ሮክ ነጭ ሙሉ ለብሱን ለብሶ መድረኩን ሲመራ «ሆሊዉድ ጥቁርን ያገለለ » ብሎታል።

እንድያም ሆኖ ይህን በመቃወም ለምን እስካሁን ድረስ ዝም አልን፤ በዚህ የሽልማት መድረክ ይህ ክስተት የመጀመርያ አይደለም ሲል ጠይቆአል።

ትችትና ቅሪታ የተፈራረቀበት የዩኤስ አሜሪካ የስዕል ጥበብና ሳይንስ ማዕከል፤ ለመጭዎቹ ዓመታት ያለበትን ስህተት እንደሚያርምና እስከ ጎርጎረሳዉያኑ 2020 ዓ,ም በመድረኩ የሚቀርቡት ሴቶችና ሌሎች እስከዛሬ ተመርጠዉ በስፋት ተመርጠዉ የማያዉቁ የጥበብ ሰዎች በእጥፍ እንደሚጨምር አስታዉቋል።

ሞጋቾች የተሰኘዉን ፊልም በመሥራቱ የሚታወቀዉ ወጣት የፊልም ሰራተኛ ክብርዓለም ፋንታ የኦስከር ሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሰርዓቱን ተከታትሎአል። የዘንድሮዉ አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት ይላል ይላል ወጣት ክብረዓለም ፤ ብዙ ታዳሚ ያልነበረዉ የሽልማት አሰጣጡም በእኩልነት ላይ ያልተመሰረተ ነበር ቢሆንም ይህ ነጥብ በፊትም የሚነሳ ነበር ሲል ገልጾልናል። ሙሉ ቃለ-ምልልሱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic