8ኛው የጣና ፎረም በባሕር ዳር | አፍሪቃ | DW | 04.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

8ኛው የጣና ፎረም በባሕር ዳር

የአፍሪካ ቀንድ አገራት ውስጣዊ መፍረክረክ እንደጠናባቸው በጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው ጣና ፎረም አስታወቀ። በምሥራቅ አፍሪካ አገራት ዘንድ የአካታች አስተዳደር እጦት እና ጎሳን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ የመጠቀም አዝማሚያ መበርታቱን ባወጣው ሰነድ አትቷል። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:09

8ኛው የጣና ፎረም በባሕር ዳር እየተካሔደ ነው

የአፍሪካ ቀንድ አገራት ውስጣዊ መፍረክረክ እንደጠናባቸው በጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው ጣና ፎረም አስታወቀ። ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ በይፋ የተጀመረው እና የኢትዮጵያ ርዕሰ-ብሔር ሣህለወርቅ ዘውዴ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋቂ ማኅማትን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የታደሙበት ይኸው ስብሰባ በምሥራቅ አፍሪካ አገራት ዘንድ የአካታች አስተዳደር እጦት እና ጎሳን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ የመጠቀም አዝማሚያ መበርታቱን ባወጣው ሰነድ አትቷል። 

ሰነዱ ፖለቲካዊ አስተዳደር በማሕበራዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ያለበት የአካታችነት ሒደት እንዲሁም በበርካታ አገራት የስልጣን ክፍፍል ጠባይ እና ጥራት በአገሮች ውስጥ እና በአገሮች መካከል የደም አፋሳሽ ግጭት መነሾ ሆኖ ሊቀጥል እንደሚችል አስጠንቅቋል። 

ውይይቱ በዛሬው ዕለት በይፋ ሲጀመር ያነሳቸው በጎ ጉዳዮች መኖራቸው አልቀረም። የኢትዮጵያ ርዕሰ-ብሔር ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሥልጣኑን ለማስረከብ መስማማቱን አድንቀዋል።የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋቂ ማኅማት በበኩላቸው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎችን አወድሰዋል። 

ዓለምነው መኮንን
እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic