78ኛው የኢትዮጵያ የድል ቀን | ኢትዮጵያ | DW | 05.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

78ኛው የኢትዮጵያ የድል ቀን

የኢትዮጵያ አርበኞች ከአምስት ዓመታት ዉጊያ በኋላ የኢጣሊያ ወራሪ ጦርን ድል ያደረጉበት 78ኛ ዓመት በዓል ዛሬ በመላዉ ኢትዮጵያ ተከብሮ ዋለ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:11

78ኛው የኢትዮጵያ የድል በዓል


የኢትዮጵያ የጥንት አርበኞች ወራሪዉን የኢጣሊያ ጦር ድል ያደረጉበት 78ኛ ዓመት ዕለት ዛሬ ተከበረ። በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሀውልት ዙሪያ በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔርና የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የበላይ ጠባቂ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፤ የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማሕበር ፕሬዝደንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ አርበኞችና ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል። የአድዋ ድልን ጨምሮ አዲስ የመታሠቢያ አደባባይ እንደሚታነፅም በስነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል። 

ወይዘሮ ሳሕለ ወርቅ ለእድምተኛዉ ባደረጉት ንግግር ዕለቱን፣ በኢትዮጵያዉን መካከል ልዩነት ቢኖርም በሐገር ጉዳይ ልዩነት እንደሌላቸዉ ያስመሰከሩበት ነዉ ብለዉታል።በበዓሉ ላይ የተካፈሉ ጥንታዊ አርበኞች በበኩላቸዉ የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ለሐገሩ ነፃነትና ክብር የነሱን አርዓያ እንዲከተል አደራ ብለዋል።ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት ከወረረችበት ከ 1928 ጀምሮ ድል ሆና እስከተባረረችበት እስከ 1933 ድረስ ኢትዮጵያዉያን አርበኞች ለነፃነታቸዉና ለክብራቸዉ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉበትን ዉጊያና ትግል አድርገዋል። 
 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

 ነጋሽ መሐመድ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic