746 ታራሚ እና ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ መወሰኑ | ኢትዮጵያ | DW | 08.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

746 ታራሚ እና ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ መወሰኑ

ከመካከላቸው በፌደራል ደረጃ በሽብር፣ በሀይማኖት አክራሪነት እና በሌሎችም የተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ 417 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ መወሰኑን አቃቤ ህግን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 01:36

ከሚለቀቁት ዉስጥ እስክንድር ነጋና አንዷዓለም አራጌ አሉበት ተብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት 746 ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎችን ለመልቀቅ መወሰኑን ዛሬ አስታውቋል። ከመካከላቸው በፌደራል ደረጃ በሽብር፣ በሀይማኖት አክራሪነት እና በሌሎችም የተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ 417 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ መወሰኑን አቃቤ ህግን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ከነዚህም ውስጥ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ እንደሚገኙበት ተገልጿል። ከዚህ ሌላ የ329 ተጠርጣሪዎች ክስ እንዲቋርጥም ተወስኗል ተብሏል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ልኮልናል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ 

Audios and videos on the topic