73 ኛዉ የኢትዮጵያ የአርበኞች የድል ቀን መታሰብያ | ባህል | DW | 08.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

73 ኛዉ የኢትዮጵያ የአርበኞች የድል ቀን መታሰብያ

ሚያዝያ 27፤ 73ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች በዓል በአራት ኪሎ የድል አደባባይ በደማቅ ስነ- ስርዓት ተከብሯል። በተለይ በብሄራዊ ትያትር አባት አርበኞች፤ ህጻናት ቲያትረኞች፤ ሙዚቀኞች የተሳተፉበት ሥነ-ስርዓት እጅግ የደመቀና ታሪክና ባህልን ያካተተ መሆኑ ተነግሮለታል።

የኢትዮጵያ አርበኞች፤ ለሃገር ነጻነት፣ አንድነትና ክብር፤ የኢጣልያ ፋሽስት ወራሪ ሃይልን በመመከት፤ ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመጉረፍ ጠላትን ያስጨነቀበት እና ድል ያደረገበት አልበገር ባይነትን ያስመሰከሩበት «የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች የድል ቀን መታሰብያ» ሚያዝያ 27፤ ለ73 ኛ ግዜ ተከብሮአል። ጥንታዊ ጀግና አርበኞች የጣልያንን ጦር አምስት ዓመት ተጋድለዉ የሃገር ነፃነትን ማስከበራቸዉ፤ አኩሪ ድል የመቀዳተቻዉን ታሪክ ህያዉ አድርጎ ለማቆየት፤ የአሁኑ ትዉልድ በተለያዩ ስነ-ፅሁፎች፤ በሙዚቃና ቀረቶዎች፤ በዉዝዋዜና በአልባሳት እንዲሁም በፊልም እና ትያትርን

በመሳሰሉ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች ሲያስታዉስና ታሪክ ሲማማርበት ይታያል።

ሚያዝያ 27፤ 73ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች በዓል በአራት ኪሎ የድል አደባባይ በደማቅ ስነ- ስርዓት ተከብሯል። ከአዲስ አበባ አራት ኪሎ ድል አደባባይ ከተከናወነዉ የአከባበር ሥነ- ሥርዓት ባሻገር፤ ቀኑ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ታስቦ ነዉ የዋለዉ። በተለይ በብሄራዊ ትያትር አባት አርበኞች፤ ህጻናት ቲያትረኞች፤ ሙዚቀኞች የተሳተፉበት ሥነ-ስርዓት እጅግ የደመቀና ታሪክና ባህልን ያካተተ መሆኑ ተነግሮለታል። ሶስተኛዉ ዝክረ አድዋ የኪነ- ጥበብ ፊስቲቫል በሚል «ኬር ኢቬንትስ እና ኮሙኒኬሽን» ድርጅት በብሄራዊ ትያትር የአርበኞች የድል ቀን መታሰብያን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሮአል። የኬር ኢቨንት ዋና ተጠሪ አቶ መሃመድ ካሳ የፊስቲቫሉ አላማ፤ የቀኑን ታሪካዊነት በባህላዊ ፉከራ፤ ቀረርቶ፤ ግጥምና ሙዚቃ እንዲሁም በአለባበስ ባህል ማክበሩ፤ ለሃገሪቱ የቱሪስት መስብዕነት ብሎም ታሪክን ለዓለም በማሳወቁ ረገድ ትልቅ ሚና ያለዉ በመሆኑ፤ ቀኑ በተዋጣለት ዝግጅት በብሄራዊ ትያትር መድረክ መከናወኑን ገልፀዋል።
በመድረኩ ከቀረቡት ታሪካዊ የኪነ- ጥበብ ትርኢቶች መካከል፤ ገብርኤላ የተባሉት ክልስ ጣልያንያዊት ዘራፍ ሙዚቃን በመድረኩ አቀንቅነዉ ተመልካችን ማስደመማቸዉ ተነግሮላቸዋል።
በብሄራዊ ትያትር የተካሄደዉን 73 ኛዉ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች የድል ቀን መታሰብያ ዝግጅትን የተከታተለዉ ታዋቂዉ ገጣሚ አበባዉ መላኩ እንደሚለዉ፤ የአርበኞች ቀንን ሥናስብ፤ ቀኑን ሥራ ባለመግባት ብቻ ሳይሆን፤ የአባት አያቶቻችን ሥራ በተለያዩ ዝግጅቶች በማሰብ እና ታሪኩን በማንሳት ለተተኪዉ ትዉልድ በማስተማር መሆን ይሆርበታል ሲል ተናግረዋል።
በጥንታዊ የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ዉስጥ የሚገለግሉትና የአርበኛ ልጅ የሆኑት ወሮ አስቴር መልኬ በበኩላቸዉ የዘንድሮዉ የአርበኞች በዓል አከባበር ከምግዜዉም በላይ ደማቅ እንደነበር ገልፀዉ፤ በተለይ እንደጥንቱ ለጀግኖች አያት አባቶች ፍሬዳዉ ተጥሎ፤ ጠጅ ቀርቦ በድምቀት ቀኑ ታስቦ መዋሉን ገልፀዋል። በኢትዮጵያ ጥንታዊ አርበኞች ጽ/ቤት በሂሳብ ሃላፊነት የሚያገለግሉት፤ ወ/ሮ አስቴር መልኬ፤ በአርበኛ አባታቸዉ ጥያቄ፤ በቀጣይ፤ አባት አርበኞችን ለማገልገል ጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ቢሮ፤ መግባታቸዉን ገልፀዉልናል።


የዛሩ ሶስት ወር አዲስ የተመረጡት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝደንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ የዘንድሮዉ የድል ቀን አከባበር ከምንግዜዉም በላይ ደማቅ የነበረ፤ በአከባበር ሥነ-ስርአቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፤ ከአስራ ሁለት የሚበልጡ አንባሳደሮች የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አርበኞችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እንደነበር ገልፀዋል። ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ ለሃገራቸው የተዋደቁ አርበኞች የሚያገኙት የጡረታ ገንዘብ እንዲሻሻል ሲሉ መጠየቃቸዉንና፤ ለኢትዮጵያዉያን አርበኞች ለሚደረግ ድጎማ መንግሥት በዓመት ለድርጅቱ አምስት ሚሊዮን ብር እንደሚያገኝ ገልፀዉልናል። ለጥንታዊ የኢትዮጵያ አርበኞች የሚሰጠዉ ድጎማ ላይ ጭማሪ ለማድረግ የቅየሳ ሥራ ላይ መሆኑንም ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተናግረዋል።
የ 85 ዓመቱ አርበኛ ሻለቃ ደጀኔ መሸሻ በበኩላቸዉ ያ የግፍ ግዜ አልፎ ለዚህ በመብቃታቸዉ ደስተኛ መሆናቸዉን፤ በመናገር የጀግንነት የፉከራ ግጥምች ደርድረዉልናል።
ብሄራዊ ትያትር በተዘጋጀዉ በ73 ኛዉ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች የድል ቀን መታሰብያ ሥነ-ስርአት ላይ በቀረርቶ አቀራረባቸዉ ተመልካችን ያስደመሙት ከያኒ ጋሻዉ አብቴን ቀረርቶ አካተናል፤ ለዝግጅቱ መሳካት ትብብር ያደረጉልንን በሙል እናመሰግናለን።

ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ይከታተሉ!


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic