63 ኛዉ አለማቀፉ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ በፍራንክፈት | ባህል | DW | 13.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

63 ኛዉ አለማቀፉ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ በፍራንክፈት

በአለም ግዙፉ እንደሆነ የሚነገርለት በጀርመን የፍራንክፈርቱ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ ከአለም ዙርያ የተሰባሰቡ ሰባት ሽህ ያህል የመጽሃፍ አሳታሚዎችን እና አቅራቢዎችን ስራ አሰባስቦ ትርኢቱን ጀምሮአል።

default

ዘንድሮ ለስድሳ ሶስተኛ ግዜ ለአምስት ቀናት የሚዘልቀዉ ይኸዉ አመታዊ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ ዘንድሮ በአለማችን በፖለቲካ ረገድ ብዙም ችግር የማይታይባትን አገር አይስላንድን በዋና እንግድነት ይዞ ቀርቦአል። የፍራንክፉርቱ አዉደ ርዕይ በአብዛኛዉ የሚታወቀዉ ጸሃፍት በሚኖሩበት አገር የስነ ጽሁፍ ስራቸዉ ባለዉ ወቅታዊ ሁኔታ በአለም አንባብያን ዘንድ ሳይታወቁ በመቅረታቸዉ በአለም የስነ ጽሁፍ እና አንባብያን ዘንድ ለማስተዋወቅ የሚደረግ መድረክ ነዉ። ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያኑ አመት እና በዚህ አመት መጀመርያ ላይ በእስላንድ የፈነዳዉ እሳተ ጎመራ የተፋዉ የአመድ ደመና የሰሜን አዉሮጻን የአየር በረራዎች ለቀናቶች በምድር እንዲቆዪ ማድረጉ እና በርካታ ተጓዦች በተለያዩ የአየር ጣብያዎች ተስተጋጉለዉ መቆየታቸዉ አይስላንድ በአለም አቀፍ የብዙሃን መገናኛ በዋና ርዕስነት እንድትነሳ ማድረጉ አይዘናጋም። ዘንድሮ ታድያ በፍራንክፈርቱ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ ላይ ከበርካታ የአይስላንድ የስነ ጽሁፍ ስራዎች በተጨማሪ አርባ ያህል የአይስላንድ ደራስያን መገኘታቸዉ ተነግሮአል። በመጭዉ ሁለት እና ሶስት ወራት ዉስጥ ሁለት መቶ የአይስላንድ የስነ ጽሁፍ ስራዎች በጀርመንኛ ተተርጉመዉ በጀርመን ለአንባብያን እንደሚቀርቡም ተገልጾአል። 318.000 ነዋሪዎችን ያቀፈችዉ እና በአዉሮጻ ሁለተኛዋ ትልቋ የአዉሮጻ ደሴት በመባል የምትታወቀዋ አገረ አይስላንድ በስፍት ከአዲስ አበባ ከተማችን በአምስት ግዜ እጥፍ በማነስዋ በአዉሮጻ

Sagenhaftes Island NO FLASH

ከሚገኙ አገሮች ዉስጥ ህዝቦች በጣም ተቀራርበዉ የሚኖሩባት አገር በመሆንዋም ትታወቃለች። በነገራችን ላይ አይስላንድ ከአዉሮጻ በስፋት ሁለተኛዋ ደሴት ስትሆን በአዉሮጻ ትልቋ ደሴት አገር ታላቅዋ ብሪታንያ መሆንዋ ይታወቃል። በለቱ ቅንብራችን የዘንድሮዉን የጀርመን ምርጥ የልብወለድ መጽሃፍ ደራሲንም እናስተዋዉቃለን። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ

Audios and videos on the topic