62ኛዉ አለማቀፍ የፊልም ትዕይንት በበርሊን | ባህል | DW | 16.02.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

62ኛዉ አለማቀፍ የፊልም ትዕይንት በበርሊን

ስድሳ ሁለተኛዉ የበርሊኑ አለማቀፍ የፊልም መድረክ የሆሊዉድዋን ኮከብ የፊልም ተዋናይ እና የኦስካር ተሸላሚ Meryl Streep በፊልም ስራ ረገድ ላበረከተችዉ አስተዋጽኦ የክብር ሽልማትን አበርክቶአል።

በርሊናል የተሰኘዉ የጀርመን አመታዊዉ አለማቀፍ የፊልም ትዕይንት ባለፈዉ ሳምንት ሃሙስ፤ ጀርመን መዲና በርሊን ላይ ተጀምሮአለ። ለአስር ቀናት የሚዘልቀዉና የፊታችን እሁድ ምሽት የሚጥናቀቀዉ ይህ ትዕይንት ስለፈረንሳይ አብዮት በሚተረከዉና ጀርመናዊትዋ ዕዉቅ የፊልም ተዋናይ ዲያና ክሩግ በዋና ገጸ- ባህሪነት የምትጫወትበት ፊልምን በማሳየት ነዉ የጀመረዉ። በጀርመንኛ ስያሜዉ  Leb wohl, meine Königin  ንግስቴ ደህና ይሁኑ ከተሰኘዉ ከዚህ ፊልም ጋር  አስራ ስምንት የተለያዩ አገራት  ፊልምች  ወርቅማ እና ብርማዉን የበርሊናለ ፊልም ማዕከል  የድብ ቅርጽ ሽልማት ለመዉሰድ ለዉድድር ቀርበዋል።

በመዲና በርሊን በሚገኘዉ በረሊናለ የፊልም መዕከል ለአስር ቀናት የሚዘልቀዉን የፊልም ትዕይንት መርቀዉ የከፈቱት የጀርመን የባህል ሚኒስትር ቤርንድ ኖይማን የብርሊኑ ከንቲባ ክላዉስ ቮቨራይት እና የፊልም ማዕከሉ ተጠሪ ዲተር, ኮሲሊክ ናቸዉ።

62ኛዉ አለማቀፍ የፊልም ፊስቲቫል ከ 67 የተለያዩ የአለም አገራት የቀረቡ  395 ፊልሞች ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን እስካሁን 35,000አስራ የፊልም ቤት መግብያ ትkvቶች መሸጣቸዉ  ተንግሮአል። ለዉድድሩ የቀረቡት በጀርመን የተሰሩ ፊለሞችም ለሽልማት ይበቁ ይሆናል ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ። በአለሙ የፊልም መድረክ እጅግ ታዋቂ የሆኑት አሜሪካዉያኑ የፊልም ተዋናያ ጥንዶች አንጀሊና ጁሊና ብራድ ፒት በበርሊናለዉ የፊለም መዐከል ከመገኘታችቸዉ ሌላ እጅግ የበርካቶችን የፊልም አፍቃሪዎች ቀልብ ስበዉ ነዉ የሰነበቱት። በአለማችን ግዙፍ የፊልም አምራች መሆኑ ከሚታወቀዉ ከዩናይትድ ስቴትሱ የፊልም ኩባንያ ሆሊዉድ ከሚያቀርባቸዉ የተለያዩ የልብ ወለድ ትረካ ፊልሞች ሌላ በአሁኑ ወቅት ጥንካራ መልክቶችን ያዘሉ ፊልሞች በአለም የፊለም መድረክ ላይ እየቀረቡ መሆናቸዉ የፊልም ተመልካቹን ቀልብ እየሳቡ መሆኑ ተመልክቶአል። የለቱ  መሰናዶ በበርሊናለዉ የፊልም ትዕይንት ዙርያ ያቆየናል. ስድሳ ሁለተኛዉ የበርሊኑ አለማቀፍ የፊልም መድረክ የሆሊዉድዋን ኮከብ የፊልም ተዋናይ እና የኦስካር ተሸላሚ Meryl Streep በፊልም ስራ ረገድ ላበረከተችዉ አስተዋጽኦ የክብር ሽልማትን አበርክቶአል።

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለስ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 16.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/144HC
 • ቀን 16.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/144HC