60 አመት ያስቆጠረዉ የናዚ ወንጀለኞች ፍርድ | የጋዜጦች አምድ | DW | 29.09.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

60 አመት ያስቆጠረዉ የናዚ ወንጀለኞች ፍርድ

እ.አ 1946 መስከረም 20 ከስልሳ አመት በፊት ልክ በዛሪዉ እለት ነበር፣ የጀርመኑ የናዚ ፓርቲ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ያገኙት

የዩኤስ አሜሪካ፣ የብሪታንያ ፣የፈረንሳይ እና የቀድሞዋ ሶብየት ህብረት ዳኞች በህብረት በመሆን ነበር ፍርድ ለመስጠት የተቀመጡት። የፍርዱ የተካኤደዉ በዝግ ችሎት ነበር። ለመጀመርያ ግዜ፣ የጦር ወንጀለኞችን እና የህዝብን እልቂት ባደረሱት ላይ በፍርድ ምላሻቸዉን ለመስጠት! በፍርዱ ሂደትም የስልክ መስመሮች ተቋርጠዋል!

የሁለተኛዉ አለም ጦርነት ከተጠናቀቀ በኻላ ጀርመንን ተከፋፍለዉ ያስተዳድሩዋት የነበሩት አራቱ አገራት፣ ማለትም የዩኤስ አሜሪካዉ፣ የፈረንሳዩ፣ የብሪታንያዉ እና የቀድሞዋ ሶብየት ህብረት የጋራ ትብብር አላማ፣ የናዚ የጦር ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ ነበር። ነገርግን ቀንደኛዉ ሂትለር እና ተከታዩ Goebbel የራሳቸዉን ነፍስ በማጥፋት ከፍርዱ ተሰወሩ። የአየር ሃይል ሚኒስትሩ የሂትለር ቀኝ እጅ የነበረዉ፣ Hermann Göring ቤተሰቦቹን እና ቁሳቁሱን በ 17 መኪና ጭኖ ሲፈረጥጥ ነበር በአሜሪካን ወታደሮች በአዉስትርያ ዉስጥ በምትገኝ Kitzbühl ከተማ መያዙን፣ የቢቢሲ የራድዮ እንዲህ ሲል ያበሰረዉ።
«Göring በተያዘ ግዜ ለብሶ የነበረዉ፣ የናዚን አርማ ያለበት እና በራሱ ስም የሰየመዉን ልዩ የናዚ የታንከኛ የክፍለ ጦር መለዮ ነበር»
የሶብየት ህብረቱ ዳኛ ኒኮታሼንኮ ህዳር 20 እንደ አዉሮፓዉያኑ አቆጣጠር 1945 Görin የናዚ ዋና ባለስልጣን እና የጦር ወንጀለኛ ሲል ክሱን የጀመረዉ። የጨካኙ እና የአረመኔዉ የናዚ ጦር መሰብሰብያ በነበረዉ በኑረንበርግ ነበር የተከሳቾቹም ፍርድ የተካሄደዉ። ፍርዱ ዋና የክስ ነጥቦችም
1. ሰላምን በመንሳት ወንጀል
2.ጦርነት በማንሳት እቅድ
3.በጦር ወንጀለኝነት እና በጦርነት ግዜ ያለ ዉልን በመሳት
4.ሰብአዊ-መብት ገፈፋ የሚሉትን ያጠቃልላል።
ቀንደኛዉ ተከሳሽ Hermann Göring ለፍርድ በዳኞች ፊት በቀረበበት ግዜ ምንም አይነት ወንጀል አልሰረሁም ሲል አስተባብሏል።
የተከሳሽ ጠበቆች ፍርዱን በመጻረር፣ ከዚህ በፊት ምንም አይነት ህግ ስላልነበረ በዳኞች ቢፈረድም ፍርዱ ህጋዊነት የለዉም! ፍርዱ መጽናት አይችልም! ይህ ህግ የወጣዉ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኻላ ነዉ ሲሉ ተከሳሾችን ነጻ ለማዉጣት ጥረዉ ነበር። የብሪታንያዉ ዳኛ ግን በዚህ ጉዳይ ጀርመን በአገሮች መካከል በሚፈጠረዉ ዉጥረት በሰላም ለመፍታት አለም አቀፉን ዉል ገቢራዊ ለማድረግ ሃላፊነት ወስዳለች ሲሉ ነበር ለይግባኙ መልስ የሰጡት።
በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ግዜ ፖላንድን በመቆጣጠር የፖላን አስተዳዳሪ የነበረዉ ጀርመናዊዉ Hans Frank የፖላንድን ፖለቲከኞችን በመረሸን፣ ይሁዶችን በመጨፍጨፍ፣ የአገሪቷን ዜጎችም በማስገደድ ወደ ጀርመን በማምጣት እና በጦር መሳርያ ምርት በማሰማራት ነበር ክስ የተመሰረተበት።
ጀርመናዊዉ Hermann : የሂትለር ልዩ ባለስልጣን የነበር ቢሆንም በአይሁዶች የግፍ ጭፍጨፋ እጄን አልጨመርኩም ሲል ተሟግቷል። በንግግሩም፣ እንዲህ አይነቱን በህዝብ ላይ የተደረገ የግፍ ጭፍጨፋ አጥብቄ እቃወማለሁ፣ አይምሮዪም ሊቀበለዉ አይችልም፣ ሲል ነበር በማስመሰል የተናገዉ። ነገርግን Göring የአለም አቀፉ የጦር ፍርድቤት፣ በአራቱም የክስ ነጥብ ወንጀለኝነቱን በመረጋገጡ በስቅላት እንዲቀጣ ፈርዶበታል። የስቅላት ቅጣቱም ሊፈጸም አንድ ሰአት ሲቀረዉ ነበር መርዝ ጠትቶ ሞቶ የተገኘዉ።
የአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት፣ በአስራሁለት ተከሳሾች ላይ፣ የሞት ፍርድ፣ ሰባቱ እድሜ ይፍታ እስር፣ ሶስቱን ደግሞ ከወንጀል ነጻ አድርጎአል። ከዚህ የፍርድ ሂደት ወዲህ ግን፣ የአራቱ አገር ዳኞች በአንድነት ምንም አይነት የፍርድ ዉሳኔ አልሰጡም። አሜሪካ ትቆጣጠረዉ በነበረዉ የጀርመን ክልል፣ የአሜሪካዉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ግን በተጨማሪ፣ በ12 የክስ ሂደት 185 ተከሳሾችን አቅርቦ፣ 24 ቱን በሞት ፍርድ ቀጥቶአል። ከተከሳሾች መካከል የናዚ አባላት፣ የህክምና አዋቂዎች፣ የህግ ባለሞያዎች፣ የባንክ ቤት ሰራተኞች ነበሩ። በዚህ የግፍ ዘመን የፍርድ ሂደት ለመጨረሻ ግዜ እ.አ 1949 በ መጋቢት ወር ነበር የፍርድ ሂደቱ የተጠናቀቀዉ።