1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«6ኛው ዙር ድጋሚ እና ቀሪ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል» ኢሰመኮ

ሰኞ፣ ሰኔ 24 2016

የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ሶማሊ፣አፋር እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሰኔ 16/2016 የተካሄደው ቀሪና ድጋሚ ምርጫ የሰብአዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ እንዲካሄድ ክትትል ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም 31 ባለሙያዎችን መድቦ በ201 ምርጫ ጣቢያዎችን ምልታ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4hjSI
«6ኛው ዙር ድጋሚ እና ቀሪ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል» ኢሰመኮ
«6ኛው ዙር ድጋሚ እና ቀሪ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል» ኢሰመኮ ምስል Negasa Desalegn/DW

«6ኛው ዙር ድጋሚ እና ቀሪ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል» ኢሰመኮ

6ኛው ዙር ድጋሚ እና ቀሪ ምርጫ  ሠላማዊና ሰብአዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ መካሄዱን ኢሰመኮ አስታወቀ

ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በአራት ክልሎችየተካሄዱ ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በአብዛኛው አካባቢዎች ሠላማዊ እና ሰብአዊ መብቶችን መርሆችን ባከበረ መልኩ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሰብአዊ  ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶችን ክትትል ለማድረግ በ201 የምርጫ ጣቢያዎችም የድምጽ አሰጣጥ ሂዴት መመለከቱን ትላንት ባወጣው ዘገባ አመልክተዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ በግጭት ወቅት በነበረው  ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  በአብዛኛው አካባቢዎች የምርጫ ጣቢያዎች  በተረጋጋ ሁኔታ ምርጫው መከናወኑን አመልክተዋል፡፡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ከመካሄዱ አንድ ቀን አስቀድሞ በሰጠው መግለጫ በመተከል ዞን አራት ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 40 የሚደርሱ ምርጫ ጣቢያዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት ምርጫ እንደማይካሄድ ገልጾ ነበር፡፡ ሰኔ 16/2016 በምርጫ ዕለት በሁሉም አካባቢዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂዴት ሰላማዊ በሆነ መልኩ መካሄዱን ቦርዱ ገልጸዋል፡፡

በ201 የምርጫ ጣቢያዎች ክትትል ተደርጓል

የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ሶማሊ፣አፋር እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሰኔ 16/2016 የተካሄደው ቀሪና ድጋሚ ምርጫ የሰብአዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ እንዲካሄድ ክትትል ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም 31 ባለሙያዎችን መድቦ በ201 ምርጫ ጣቢያዎችን ምልታ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡ ለረጅም ዓመታት በጸጥታ ችግር ውስጥ በቆየው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር ምርጫ ሳይካሄድባቸው በከቀሩ ጣቢያዎችዎች በስተቀር በአብዛኛው አካባቢዎች በተረጋጋ ሁኔታና አሳሳቢ የጸጥታ ችግር ሳይደርስ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡  ሰኔ 16 በተካሄደው ምርጫ ላይ ከተሳተፉት ፓርቲዎች መካካል የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አንዱ ሲሆን በተወዳረባቸው መተከል እና ካማሺ ዞን ወረዳዎች ምርጫው  ሠላማዊ በሆነ መንገድ  መጠናቀቁን ለዲዳቢሊው ተናግረዋል፡፡

«6ኛው ዙር ድጋሚ እና ቀሪ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል» ኢሰመኮ
«6ኛው ዙር ድጋሚ እና ቀሪ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል» ኢሰመኮ ምስል Negasa Desalegn/DW

ቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በበኩሉ በአሶሳ እና መከተል ዞን በምርጫ ላይ መሳተፉን ገልጸዋል፡፡በተለይም በመተከል ዞን ዳንጉር በተባለ ወረዳው ምርጫ ከመካሄዱ 1 ቀን አስቀድሞ በተከሰተው ግጭት በሰው ህይወት ማለፉን እና በወረዳው በተካሄደው ምርጫ ራሱን ማግለሉን የፓርቲው ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ተሰማ  አመልክተዋል፡፡

ከ2011 ዓ.ም አንስቶ በተለያዩ ወቅቶች በአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ወይም በኮማንድ ፖስት ሲተዳደር በነበረው የመከተል ዞን 7 ወረዳዎች ውስጥ በዕለቱ ምርጫ  ሠላማዊ በሆነ መልኩ መካሄዱን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አትንኩት ሽቱ አስታውቋል፡፡ በዞኑ በስምንት ምርጫ ክልሎችና 260 ምርጫ ጣቢያዎች ያለምንም ጸጥታ ችግር መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

የኢትየጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ምርጫው በተካሄደበት ዕለት ሰኔ 16/2016 ዓ.ም  ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ ምርጫው በስኬት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ከምርጫ ቀን ቀደም ብሎ 2 ምርጫ ጣቢያዎች በሚገኙበት አካባቢ ግጭት ተከስቶ እንደነበር የተናገሩ ሲሆን በወረዳው በሚገኙ ከ33 ምርጫ ጣቢያዎች በ31 ጣቢያዎች ከጠዋት ጀምሮ ምርጫ መካሄዱን እና በአንድ ምርጫ  ጣቢያ ደግሞ በቁሳቀስ መዘግየት ምክንያት ሰኞ ዕለት ምርጫ እንደሚካሄድ ገልጸው ነበር፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ዮኃንስ ገብረእግዚአብሔር