54 ኢትዮጵያዉያን በኬንያ ታሰሩ | ኢትዮጵያ | DW | 11.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

54 ኢትዮጵያዉያን በኬንያ ታሰሩ

የኬንያ ፖሊስ በሕገ- ወጥ አገሪትዋ ዉስጥ የሚኖሩ ያላቸዉን 54 ኢትዮጵያዉያን ማሰሩ ተመለከተ። እንደ ፖሊስ ገለጻ፤ በኬንያ ናይሮቢ ካሳራኒ በሚባል አካባቢ ሦስት ክፍል ዉስጥ ሲኖሩ የነበሩ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን የተያዙት ፖሊስ በደረሰዉ ጥቆማ እንደሆነ ገልጾአል።

ነዋሪዉ እንዲህ ዓይነቱን ሕገ-ወጥ ነገር መጠቆሙ ለራስ ደሕንነት ነዉ ሲል፤ ማወደሱም ተዘግቦአል። ከአስር ወር በፊት እዚያዉ ኬንያ ናይሮኒ ዉስጥ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመጓዝ ዝግጅት ላይ የነበሩ 101 ኢትዮጵያዉያንን ፖሊስ መያዙን ማስታወቁ አይዘነጋም።

ፋሲል ግርማ

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic