1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

5ኛዉ የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ኅብረት ጉባኤ

ሐሙስ፣ ኅዳር 21 2010

ከሁለት ዓመት በፊት የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ መንግሥታት መሪዎች ማልታ ላይ ተሰባስበዉ ነበር። ከትናንት ጀምረዉ ደግሞ አቢዦን ኮትዴቩዋር ተገናኝተዋል። ከማልታዉ ንግግር በኋላ የደረሱባቸዉን አንዳንድ የስምምነት ነጥቦች በሥራ ላይም አዉለዋል።

https://p.dw.com/p/2oXMV
Elfenbeinküste EU-Afrika-Gipfel | Angela Merkel
ምስል picture alliance/dpa/Bundesregierung/G. Bergmann

ጉባኤው ስደትን ለመግታት እና ፀጥታን ለማጠናከር ተስማምቷል፤

ለሁለት ቀናት ያካሄዱት ጉባኤ የጋራ ትብብር ላይ ያተኩራል ቢባልም ዋና ትኩረቱ ስደትን መገደብ ላይ እንደሆነ ነዉ የሚነገረዉ። ከ80 የሚበልጡ ሃገራት መሪዎች በተሳተፉበት በዚህ ለአምስተኛ ጊዜ በተካሄደዉ የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ሃገራት ጉባኤ ማጠቃለያ ላይም በስደት እና በፀጥታ ጉዳይ ላይ ትብብራቸዉን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል። የወጣት ትዉልዷ ቁጥር እያደገ መሄዱ የሚነገርላት አፍሪቃ የሥራ ዕድሎችን ማስፋፋት እስካልቻለች ድረስ ግን የስደት ጉዳይ አሁንም አሳሳቢ እንደሆነ እንደሚቀጥል ነዉ የሚነገረዉ። የዶቼ ቬለዋ ባርባራ ቬዝል የጻፈችዉን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ከበርሊን እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።

ባርባራ ቬዝል/ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ